የመጀመሪያው የጎዳና ላይ ፋሽን ትርኢት

የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የመጀመሪያው የጎዳና ላይ ፋሽን ትርኢት ቀረበ

***********************************************

[ነሐሴ 21/2014 ዓ/ም፤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ]

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2014 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ከሰባት በላይ በሆኑ የፈጠራ ዲዛይኖች የተሰሩ አልባሳትና ልዩ ልዩ ማስጌጫዎች የተዘጋጀ እና በአገራችን የመጀመሪያ የሆነ የተማሪዎች የጎዳና ላይ ፋሽን ትርኢት በውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ አቅርበዋል:፡

ዝግጅቱን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ብርሃን ሀይሉ ተቋሙ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ትርኢት ማዘጋጀቱ ለከተማውም ሆነ በዘርፉ ላሉ አካላት ትልቅ ምዕራፍ መክፈቱን ተናግረዋል፡፡ ኩነቱም በፋሽን ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ በመሆኑ የአገራችንን ቴክስታይልና አልባሳት ኢንዱስትሪን በማሳደግ ረገድና የስራ ዕድል በመፍጠር ትልቅ አስተዋጾ እንዳለው ይታመናል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ታምራት ተስፋዬ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ24 ፕሮግራሞች የፒኤች ዲ፣ የሁለተኛ ዲግሪ አና በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ በማስተማር የባሕር ዳር ከተማን የፋሽን ከተማ ለማድረግ አልሞ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ታምራት አክለውም እነዚህ በትርኢቱ ላይ የምታዯቸው ተመራቂዎቻችን በሀገሪቱ ውስጥ ተሰማርተው ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪን ለማዘመን የሚሰሩ ልጆቻችን ናቸው ብለዋል፡፡ በዚህም ኢንስቲትዩቱ ከሚያስመርቃቸው 26% የራሳቸውን ስራ ፈጥረው የሚሰሩ ሲሆን ከ85% በላይ የሚሆኑት ደግሞ በተመረቁበት ሙያ የስራ ዕድል ማግኘታቸው እንደ ሀገር የመጀመሪያው ኢንስቲትዩት ያደርገናል ብለዋል፡፡

የዕለቱን ፕሮግራም ያስተባበሩት የፋሽን ዲዛይን ትምህርት ክፍል ኃላፊ መምህር ሰላማዊት መላኩ ተመራቂ ተማሪዎች ሀገር በቀል የሆኑ እና የውጪውን አልባሳት በማቀናጀት ያላቸውን የፈጠራ ስራ በማሳየታቸው ተቋሙንም ሆነ ዩኒቨርሲቲውን ለማህበረሰቡ በማስተዋወቅ ረገድ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በፋሽን ትርኢት ስነ-ስርዓቱ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አባላት እና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የከተማው ማህበረሰብ ታድመውበታል፡፡ የፋሽን ትርኢቱም ከስካይ ላይት ሆቴል እስከ ዩኒሰን ሆቴል ባለው የጎዳና መንገድ ላይ የተካሄደ ነበር፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ- ባዳዩ-BDU

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting, inviting and sharing our Pages!

Thank you for your likes and comments!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official

Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt

LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university

Twitter: - https://twitter.com/bdueduet

Tiktok:-https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL

website :- www.bdu.edu.et