የህግ የመውጫ ፈተና

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በብሄራዊ ደረጃ በተሰጠው የህግ የመውጫ ፈተና ከፍተኛውን ውጤት አስመዘገበ

በ2019 በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው በአገሪቱ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በወሰዱት የመውጫ ፈተና የመጀመሪያ የሆነውን ትልቅ ውጤት ያስመዘገበውን ተማሪ ጨምሮ ስድስት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህግ ተመራቂ ተማሪዎች ከመጀመሪያዎቹ ሃያ ተማሪዎች ውስጥ መሆን ችለዋል፡፡

ለዚህ አኩሪ ውጤት ምንም እንኳን በዋናነት የተማሪዎቹ ጥረት ተጠቃሽ ቢሆንም የመምህራንና በአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አስተዋፅኦም የጎላ እንደሆነ ይታመናል፤ በመሆኑም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ፣ ለዚህ ደረጃ እንዲበቁ ታላቅ ድርሻ ላበረከቱ መምህራንና በአጠቃላይ ለዩኒርሲቲው ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ ይህ ውጤት ዩኒቨርሲቲው እያደረገ ላለው ጥራት ያለው ትምህርት የማዳረስ ግቡ አንድ ማሳያ እንደሆነ ይታመናል፡፡
በዚህ የብቃት ፈተና ውጤት ያስመዘገቡት ስድስት የህግ ተመራቂ ተማሪዎች
1. ቀናው ተስፋዬ
2. ጌታሁን መንዲስ
3. ሙሉቀን ዲዱ
4. ናትናኤል ተስፋዬ
5. ኤፍሬም ገዛኸኝ
6. ሰለሞን ገዛኸኝ

ሲሆኑ ከእነዚህ ተማሪዎች ቀናው ተስፋዬ ከአጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ የመጀመሪያውን ትልቅ ውጤት 81 አማካይ ነጥብ በማስመዝገብ አንደኛ የሆነ ሲሆን፤ ጌታሁን መንዲስ በ78 ሶስተኛ እና ሙሉቀን ዲዱ ደግሞ በ76 ነጥብ ስድስተኛ በመሆን ከፍተኛ ውጤት አግኝተዋል፡፡

ተመሳሳይ ውጤቶችም ዩኒቨርሲቲው ዋና ግብ አድርጉ ባስቀመጣቸው ሌሎች ተግባራት ለምሳሌ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት እንደሚደገም በመተማመን ለዩኒቨርሲቲው ኩራት የሆኑትን እነዚህን ተማሪዎች ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ለቀጣይ ተመሳሳይ ድሎች እንዲተጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡