የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ምልከታ

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የዩኒቨርሲቲውን የበጀት አጠቃቀም አስመልክቶ ግምገማና ምልከታ አካሄደ

(ታህሳስ 12/2015 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፌዴራል መንግሥት በ2015 በጀት ዓመት የተመደበው በጀት በመመሪያው መሰረት የበጀት ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ባማከለ መልኩ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን አስመልክቶ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት እና የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡

በፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የውይይት መክፈቻ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር፣ ከምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን እና ወደፊት ሊሰሩ የታቀዱ ስራዎችን አስመልክቶ ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ እና ገለፃ አድርገዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በሀገር አቀፍ ደረጃ ትምህርት ሚኒስቴር በሰራው የተልዕኮ ልየታ ፕሮግራም መሰረት የምርምር ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲሰራ መመረጡን ጠቅሰው ሀገሪቱ ባስቀመጠችው ቀጣይ አቅጣጫ  መሰረት ራሱን የቻለ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ኮሚቴ አቋቁሞ በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴው ጠቁመዋል፡፡

ዶ/ር እስይ አክለውም ከመማር ማስተማር ስራው በተጨማሪ በጤናው ዘርፍ ከ7 ሚሊዮን በላይ ማህበረሰብን እያገለገለ ያለውን የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስራ እንቅስቃሴን እና ዩኒቨርሲቲው ከ200 በላይ የውጭ ሀገራት ጋር ያለውን አለማቀፋዊ ግንኙነትና   የተሰራውን ስራ ጠቅሰው አሁን ላይ በሦስተኛ ዲግሪ የሚሰጡ ፕሮግራሞችን 99 በማድረስ ከአንድ ሺህ በላይ  የPhD ተማሪዎችን እያሰለጠነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ደበበ አድማሱ በበኩላቸው ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፌዴራል መንግሥት በ2015 በጀት ዓመት የተመደበው በጀት በፕሮግራም በጀት አሰራርና መመሪያ መሰረት የበጀት ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን በአማከለ መልኩ መሰራቱን እና በስራ ሂደቱ የታዩ እንከኖችን በመስክ ምልከታ ወቅት የተገኙ ግኝቶች በጥንካሬ፣ በጉድለትና ቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በመለየት ቋሚ ኮሚቴው ቀድሞ በላከው ቼክ-ሊስት መሰረት የተሰሩ ስራዎችን መገምገሙን ተናግረዋል፡፡ በዚህ መሰረት ዩኒቨርሲቲው የተመደበለትን በጀት ለታለመለት አላማ በጊዜ ሰሌዳው መሰረት የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀማቸው ጥሩ  መሆኑን  ተናግረው  ቀደም ሲል ከተማሪዎች ምግብ ጋር ተያይዞ የወጡ ውስን ጨረታዎችን የፌዴራል ኦዲት መስሪያቤት  እንደ ችግር ቢያነሳም አሁን ላይ ካለው የምግብ ግብዓቶች የዋጋ ግሽበት አንፃር ሲታይ   ዩኒቨርሲቲው አሳማኝ በሆነ መልኩ መልስ በመስጠቱ የጎላ ችግር እንዳልሆነ ቋሚ ኮሚቴው መገምገሙን ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ወቀት ከግንባታ እና ከግቢ ውበት አንፃር  በበጀት ዓመቱ የተከናዎኑ ስራዎችን እና በስራ ሂደት ውስጥ ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም ለችግሮች የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን አስመልክቶ ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም የኢ.ፌ.ድ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመስክ ምልክታ ወቅት በፔዳ፣ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ፣ በBiT ግቢዎች የተሰሩ የግቢ ውበት ስራዎችን፣ የንብረትና አስተዳደር አደረጃጀትን፤ የህፃናት ማቆያ ማዕከላትን እና የጃን ሞስኮቭ ዲጅታል ቤተ-መጽሃፍትን ጎብኝተዋል፡፡

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ``

``Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

TikTok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY