ከHIV ጋር ያለው ግንኙነት ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና

የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠነው

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው ኤች/አይ/ቪ/ኤ/መከ/መቆ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ቅድመ ትምህርት ከHIV ጋር ያለው ግንኙነት ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና ከሰኔ 9 እስከ 10/2014 ዓ.ምድረስ እየሰጠ ነው፡፡

የአሰልጣኞች ስልጠናው ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ከትምህርትና ስነ-ባህሪ ኮሌጅ እና ከኤች/አይ/ቪ/ኤ/መከ/መቆ ዳይሬክቶሬት ለተውጣጡ 25 መምህራን ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ ገልፀዋል፡፡

ስልጠናውን ሲሰጡ ያገኘናቸው የህብረተሰብ ጤና ስፔሻሊስት የሆኑት አቶ ምክሩ ሽፈራው እንደተናገሩት ቅድመ ትምህርት ከHIV ጋር ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል እንዲሁም የአቻ ግፊትን እንዴት መከላከል ይቻላል፣ ከHIV አንፃር አገራችን ያለችበት ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውን በመወያየት መከላከያ መንገዶችን የተመለከቱ ሀሳቦች ላይ ስልጠናው ትኩረት እንደሚያደርግ አመላክተዋል፡፡