አረንጓዴ አሻራ በብር አዳማ

የአረንጓዴ አሻራ ጉዟችን በብር አዳማ ሰንሰለታማ ተራሮች!

(ሀምሌ 13/2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ BDU) በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት፣ ይልማና ዴንሳ እና ሰከላን አዋስኖ የሚገኘው ብር አዳማ ሰንሰለታማ ተራራ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የተራቆተውን አካባቢ በደን የመሸፈን እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ዛሬም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩን ያስጀመሩት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳት ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራው እንደተናገሩት አፈርና ውሃ ጥበቃ ከአረንጓዴ አሻራ ጋር ተያይዞ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የብር አዳማ ሰንሰለታማ ተራሮችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ በየአመቱ የሚተከሉትን ችግኞች ለመመልከት እና ህብረተሰቡን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ችግኞችን በመትከል ደኑን የማስፋት ስራ እየተሰራ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ዩኒቨርሲቲው ባስገነባው ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለው ንፁህ የመጠጥ ውሃ በቅርቡ ተጠናቆ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ አያይዘውም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን የህብረተሰቡን ችግር ሊፈታ የሚችል የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን እንደሚያከናውን ጠቁመው የወረዳ አመራሮችም ዩኒቨርስቲው ቴክኖሎጂዎችን ሲያስተዋውቅ መሬት ላይ ወርደው እንዲተገበሩ የበኩላቸውን እንዲወጡ እና የሚተከሉ ችግኞችን ደግሞ በመንከባከብ በባለቤትነት እንዲይዙ አመራርና ማህበረሰቡን አደራ ብለዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ የተገኙት የቋሪት ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ድረስ በበኩላቸው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ብር አዳማ ተራራን ከጉዳት ለመታደግ እና የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ከ30 በላይ አርሶ አደሮችን አዊ ዞን ድረስ በመውሰድ አሰልጥኖ ልምድ እንዲቀስሙ በማድረግ በተራቆቱ መሬቶች ዲከረንስ የተባለ ችግኝ በመትከል ለከሰል ምርት እንዲውልና ወጣቱን ተጠቃሚ በማድረግ ሰፊ ስራ መሰራቱን አስታውሰዋል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ-BDU

Description: 💦Description: 💦Description: 💦Description: 💧Description: 💦Description: 💦Description: 💧Description: 💦Description: 💦Description: 💦

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ

Wisdom at the source of Blue Nile

Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎

Thank you for visiting our page!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official

Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt

LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university

Twitter: - https://twitter.com/bdueduet

Tiktok:- https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL

website :- www.bdu.edu.et

#BDU60th_ANNIVERSARY