ቲማቲምን በክረምት

ቲማቲምን በክረምት የማምረት ፓይለት ፕሮጀክት ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ

*******************************************************************

(ታህሳስ 05/2015 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በፊንላድ አስተባባሪነት ከአውሮፓ ህብረት ሆራይዘን 2020 ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በሜጫ ወረዳ ቆጋ መስኖ ተፋሰስ አካባቢ  በሦስት ቀበሌዎች በተመረጡ አራት አርሶ አደሮች ማሳ ላይ በክረምት ቲማቲምን በዳስ የማምረት ዘዴ ፓይለት ፕሮጀክትን አስመልክቶ የክልል እና የወረዳ ግብርና ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው አርሶ አደሮች  በተገኙበት የመስክ ምልከታ ተካሂዷል፡፡

በመስክ ምልከታው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና እና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የሆልቲ ካልቼር (Horticulture) ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ እንዲሁም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር መልካሙ አለማየሁ በሀገራችን የቲማቲም ምርት በክረምት ወቅት አለመመረቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና ለቲማቲም ዋጋ መወደድ መንስኤ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  

ችግሩን ለመቅረፍ እና አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት  የሚሳተፉበት ሆራይዘን 2020 ፕሮጀክት በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሜጫ ወረዳ በመራዊ ከተማ አካባቢ በተመረጡ ሦስት ቀበሌዎች ላይ  ለአርሶ አደሮች ለእያንዳዳቸው 140 ሺህ ብር በላይ በማውጣት የፕላስቲክ ዳስ በማዘጋጅት እና ሦስት አይነት የቲማቲም ዝርያዎችን ከኦሮሚያ ክልል በማምጣት የምርምር ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደ ዶ/ር መልካሙ ገለጻ ቴክኖሎጂው ለሀገራችን አዲስ ቢሆንም ያደጉ ሀገራት በስፋት እንደሚጠቀሙበት ተናግረው አሁን ላይ በምናደርገው የፓይለት ፕሮጀክት አበረታች ውጤት የታየበት በመሆኑ  በቀጣይ በሌሎችም አካባቢዎች አርሶአደሩ በስፋት ሊተገብረው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር መልካሙ አክለውም ፕሮጀክቱ  ቲማቲምን በክረምት ከማምረት ቴክኖሎጂ በተጨማሪ በባቄላ ምርት፣ በአቮካዶ ምርት፣ በአሳ ምርት እና የሽንኩርት ምርቶች ለረጅም ጊዜ የማቆየት ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቲማቲም ዝርያዎችን በባለሙያ ክትትል እየተደረገላቸው ከዘሩ አርሶአደሮች መካከል አቶ ግዛት በሬ እና አቶ  አበረ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቲማቲምን በክረምት የማምረት ቴክኖሎጂ በእጅጉ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ተናግረው ከነሀሴ ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከተከሉት የቲማቲም ዝርያ መካከል ጋቢ እና ጋሊሊያ 39 የተባሉ ዝርያዎች የተሻለ ምርት እንዳላቸው  ተናግረው፤ እስካሁን በሁለት ጊዜ ለቀማ ብቻ ከ10 ሺ ብር በላይ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ እንደ አርሶአደሮች ገለፃ በምርት ሂደቱ በተክሉ ላይ የበሽታ ምልክቶች ቢታዩም የግብርና ባለሙያዎች  በሚያደርጉላቸው የሙያ እገዛ ምክንያት ችግሩን ማስወገድ መቻሉን  ተናግረዋል፡፡     

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና እና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ት/ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር እንየው አድጎ በበኩላቸው የቲማቲም ዘሩ በከፍተኛ ዋጋ ከደብረዘይት ከተማ ሲመጣ አርሶአደሩን ለመጥቀም ታስቦ በመሆኑ ገበሬዎች የግብርና ባለሙያዎች በሚሰጧቸው ምክር ተጠቅመው ቲማቲም በክረምት በማምረት ብቻ ሳይሆን ዘሩን በማፍላት እና ለገበያ በማቅረብ ብቻ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ 

`ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ``

``Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

TikTok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY