በፕ/ር ምንዳርአለው ዘውዴ የተፃፈ “ነገ መቼ ነው? ” መጽሐፍ ተመረቀ

በፕ/ር ምንዳርአለው ዘውዴ የተፃፈ “ነገ መቼ ነው? ” መጽሐፍ  ምረቃ ተካሄደ

**************************************************************

(ሀምሌ 15/2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር በሆኑት ፕሮፌሰር ምንዳርአለው ዘውዴ “ነገ መቼ ነው?” በሚል ርዕስ የተጻፈው መጽሐፍ ምረቃ እና የፕሮፌሰሩ የህይዎት ልምድ ተሞክሯቸውን ያካፈሉበት መርሃ-ግብር የባሕር ዳር ከተማ ወጣቶች፤ በርካታ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው ፔዳ ግቢ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

   በመጽሐፍ ምርቃት ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል የፅናት፣ የማይናዎጥ አቋም ተምሳሌት የሆኑትን ኩሩ ኢትዮጵያዊ ፕ/ር ምንዳርአለው ዘውዴ በአካል ተገኝተው የህይዎት ልምድና ተሞክሯቸውን እንዲያከፍሉ እና መጽሐፋቸውንም በተቋማችን እንዲመረቅ ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከቱ የማዕከሉ ሰራተኞች እና በዕለቱ የተገኙ ታዳሚዎችን አመስግነዋል፡፡

 ፕ/ር ምንዳርአለው በወቅቱ ምሁር ጠል የሆነው የአስተዳደር ስርአት ያደረሰባቸው እንግልትና ጫና ሳይበግራቸው ባልተለመደ መልኩ ወደ ገጠሪቷ የኢትዩጵያ ክፍል በመሄድ የግብርና ስራቸውን በመከወን ወንድሞቻቸውን አስተምረው ለሀገር የሚጠቅሙ ምሁራን እንዲሆኑ አስተዋፅኦ ከማበርከታቸውም በተጨማሪ በእለቱ ለምረቃ የበቃውን “ነገ መቼ ነው? ”መጽሐፍን ጨምሮ የስናዳር ስንክሳሮች፣ ራስን መሰለል፣ ሰውና ሰው እና አፍን ዘግቶ ፉጨት የተሰኙ የልቦለድ መፅሐፎችን ለአንባቢያን ማበርከታቸውን ተናግረዋል፡፡ እንደ ዶ/ር ዘውዱ ገለፃ የተማረ ሰው መልካም መልካሙን ብቻ ይዞ የሚጓዝ ሳይሆን አስቸጋሪ እና ፈታኝ ሁኔታዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ እየቀየረ የሚያድግ መሆኑን በተግባር ያሳዩ ታላቅ ሀገር ወዳድ ምሁር እና የፅናት ተምሳሌት  መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡   

   በዕለቱ የተመረቀውን “ነገ መቼ ነው? ” አዲሱ መጽሐፍ አስመልክቶ ሰፋ ያለ የዳሰሳ ጥናት  በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋና የስነ-ጹሁፍ መምህር በሆኑት በዶ/ር አንተነህ አወቀ የቀረበ ሲሆን በደራሲው ከተፃፈው ሰውና ሰው መጽሐፍ ላይ የተወሰዱ ቅንጫቢ ምንባቦችን በዶ/ር ሞገስ ሚካኤል፣ በሂሩት አድማሱ እና በሰርፀ ፈቃደ ለታዳሚዎች በንባብ  ቀርቧል፡፡

 ፕሮፌሰሩ በ1983 ዓ.ም የተደረገውን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርነታቸው መባረራቸውን ጨምሮ ለ27 ዓመት ያሳለፉትን የህይወት ውጣውረድ እና ተሞክሯቸውን እንዲሁም ለሀገር ሰላምና ለህዝብ አንድነትና ፍቅር ያላቸውን የማይናወጥ ወጥ አቋማቸውን አጋርተው ከታዳሚው ለቀረበላቸው ሀሳብና ጥያቄ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

   በመጨረሻም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕል ማዕከል እንዲሁም በባሕር ዳር ከተማ አድናቂዎች የተዘጋጀውን ስጦታ ከዶ/ር ዘውዱ እምሩ እና የሀገር ሽማግሌዎችን ወክለው ከተገኙት ከአባ መስፍን አድማሱ እጅ ፕሮፌሰር ምንዳርአለው ዘውዴ ተቀብለዋል፡፡     

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ-BDU

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank YOU for visiting and inviting our pages, for your likes and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official

Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt

LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university

Twitter: - https://twitter.com/bdueduet

Tiktok:- https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL

website :- www.bdu.edu.et