በዓለም አቀፍ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ስልጠና

በዓለም አቀፍ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ

************************************************

በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከሁሉም ግቢ ለተውጣጡ የሒሳብ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች በዓለም አቀፍ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (International Financial Reporting System) ዙሪያ ከየካቲት 12 /2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ፔዳ ግቢ በሚገኘው የስልጠና ማዕከል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲዉ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ ስልጠናው ከተለመደው የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ወጣ ብሎ የአሰራር ስርዓቱን ለማዘመን የሚሰጥ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና እንደሆነና ወደፊትም ተደራሽነቱን በማስፋት ለሌሎች ሰልጣኞች በቀጣይ ዙር ስልጠና እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው አካውንቲግንና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል መምህር ዶ/ር አጉማስ አላምረው የስልጠናውን ዓላማ ሲገልፁ በዩኒቨርሲቲውን የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ለማዘመን ታልሞ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ዶ/ር አጉማስ አክለውም ስልጠናው ዓለም አቀፋዊ ፋይዳው የጎላ ሲሆን አገራችን ኢትዮጵያ አንድ መቶ ሰልሳ ስድስት አገሮች ወደሚተዳደሩበት የሂሳብ አያያዝና የአሰራር ስርዓት ጎራ እንድትሰለፍ የማንቂያ ደወል ሆኖ እንደሚያገለግል ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች በየጊዜው ከአንዱ የስራ ክፍል ወደ ሌላው የስራ ክፍል ስለሚቀያይሩ ዩኒቨርሲቲው ለሙያዊ ስልጠና ትኩረት በመስጠት ሁሉም ሰራተኛ ስልጠና የሚያገኝበት ሁኔታ እንዲመቻች አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ሙሉጉጃም አንዱዓለም