በሰው ኃብት መረጃ አያያዝ ዙሪያ ስልጠና

በሰው ኃብት መረጃ አያያዝ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

***************************************

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ከሁሉም ግቢዎች ለተውጣጡ የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በዩኒቨርስቲው የስልጠና ዳይሬክቶሬት እና አይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በአጠቃላይ የሰው ኃብት መረጃ አያያዝ ዙሪያ ከየካቲት 15-16/2014 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በፔዳ ግቢ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናውን በመስጠት ላይ ያገኘናቸው የከፍተኛ ሲስተም አናሊስት አቶ ባወቀ ወንድም ስልጠናው ከአሁን በፊት በተለምዶ የሚሰሩትን አጠቃላይ መረጃዎች በማዘመን ሁሉም ሰራተኛ ያለምንም የቦታና የጊዜ ገደብ የሚፈለገውን መረጃ ለሚፈለገው አካል በሲስተም ለማድረስ እንዲቻል ታልሞ የሚሰጥ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አሰልጣኙ አክለውም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉ ሁሉም ግቢዎች በሰው ጉልበት የሚተላለፉ መረጃዎችን በሲስተሙ አማካኝነት የተቀናጀ ሪፖርት ለመስራት፣ መረጃዎች በአስፈላጊው የጊዜ ገደብ እንዲተላለፉ ወደ ሲስተሙ ማስገባት እንዲችሉና መረጃውንም አውርደው እንዲተገብሩ ስልጠናው በር ከፋች መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዉ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ በበኩላቸው ስልጠናው የዩኒቨርሲቲውን አጠቃላይ መረጃ ከተለምዶ አሰራር ለይቶ በማዘመንና በሲስተሙ አማካኝነት አሰፈላጊውን መረጃ በተገቢው ጊዜ ለሚመለከተው አካል ለማድረስ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  

ዘጋቢ፡- ሙሉጉጃም አንዱዓለም