በመሰረታዊ የፕሮጀክት ዕቅድ አስተቃቀድ ላይ ስልጠና ተሰጠ

በመሰረታዊ የፕሮጀክት ዕቅድ አስተቃቀድ ላይ ስልጠና ተሰጠ

**************************************************

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ስልጠና ዳይሬክቶሬት ከህግ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር መሰረታዊ የፕሮጀክት ዕቅድ አስተቃቀድ እና ሀሳቦች ዙሪያ ለመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት እና የህግ ትምህርት ቤት መምህራን የሁለት ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር   ዶ/ር ተመስገን መላኩ እንደተናገሩት ስልጠናው ከፅንሰ ሀሳብ ጀምሮ የፕሮጀክት ምንነትና ደረጃዎች እንዲሁም ፕሮጀክት ሲታሰብ ስለሚያስፈልጉ ዋና ዋና ጉዳዮች፣ አስፈላጊ መሳሪያዎች እና ክህሎቶች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደ ነበር ተናግረዋል፡፡ በዚህም ሰልጣኞች የፕሮጀክት ባህሪያት ለይተዋል፣ ፕሮጀክት ችግር መፍቻ መሆኑን አውቀዋል፣እንዲሁም ፕሮጀክት ከመደበኛ ስራ የተለየ መሆኑን ተገንዝበዋል፡፡ ይህም በሂደት ፕሮጀክት በመስራት የተቋሙን እና የማህበረሰቡን ችግሮች መፍታት ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ተመስገን አክለውም የሁለት ቀን ስልጠና በቂ ባለመሆኑ ተከታታይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ እና በተግባር የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በማሳየት ጭምር ቢታገዙ ክህሎታቸውን ያዳብራሉ፤ እንደተቋምም ፕሮጀክቶችን የመስራት አቅምን እንደሚያሳድግ ገልፀዋል፡፡

ሰልጣኞችም በስልጠናው ግንዛቤ እንደጨበጡ የጠቆሙ ሲሆን ተጨማሪ ጊዜ ለስልጠናው ቢሰጥ ስልጠናውን በጥልቀት ለመረዳት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡