በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና የምክክር መድረክ

"በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና" በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ

********************************************************************

 (ታህሳስ 24/2015 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አመራር አካላት "በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና" በሚል መሪ ቃል በሀገራዊ ችግሮች እና በመፍተሄዎቻቸው ላይ ያተኮረ ሀገራዊ ውይይት ለሁለት ተከታታይ ቀናት በጥበብ፣ በሰላም እና በፔዳ ግቢዎች የመሰብሰቢያ አዳራሾች ሲካሄዱ ቆይተው የማጠቃለያ ውይይት የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት  እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አደም ፋራህ እና የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በተገኙበት በጥበብ የመሰብሰቢያ አዳራሽ  በውይይቱ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች አቶ አደም ፋራህ  ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና በሚል መሪ ቃል ትናንት የተጀመረው የምክክር መድረክ ላይ በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚገኙ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን በውይይት መድረኩ ላይ ከኢኮኖሚ፣ ከፖለቲካ እና ከሰላም፣ ከዲፕሎማሲ እና ከውጭ ግንኙነት ጋር የተያያዙ እና በሀገር ግንባታ ላይ ምሁራን ያላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ከማን ምን ይጠበቃል በሚሉ አራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ  የተለያዩ ጥያቄዎች አተነስተዋል፡፡ ከኢኮኖሚ አንፃር ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል መንግስት ኢኮኖሚውን ለማከም የሄደበት ርቀት ምን ይመስላል፤ ኢኮኖሚው ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ ማኑፋክቸሪንግ ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበት እና በዘርፉ ምርት እና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚገቡ ስራዎችን መስራትና  በሀገሪቱ ውስጥ በየዘርፉ ያሉንን እምቅ ፀጋዎች ለመጠቀም እቅዶች ተነድፈው ወደ ትግበራ ለመግባት እንደመንግስት ምን እየተሰራ ነው? ስንዴን ወደውጭ እንልካለን ስንል የሀገር ውስጥ የስንዴ ፍለጎት ተሟልቶ ነው ወይ?  ቀደም ሲል ከዩኒቨርሲቲ መምህራን ደምወዝን ጨምሮ የተለያዩ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎችን ከመመለስ አንፃር መንግስት ምን አስቧል? የሚሉ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆኑ የሀገሪቱን የፀጥታ እና የሰላም ስራዎችን ለማረጋገጥ ከህገ-መንግስት መሻሻል ጋር ተያይዞ መንግስት ስራዎችን በቁርጠኝነት  ከመስራት  አንፃር ምን ታቅዷል? የሚሉ ጠንክር ያሉ ሀገራዊ ጥያቄዎች ከስራ ከተሳታፊዎች ቀርበዋል፡፡

ከዲፕሎማሲ እና ከውጭ ግንኙነት ጋር በተያያዘ የሀሪቱን የዲፕሎማሲ ዘርፍ እንዲመሩ በተለያዩ ሀገራት የሚመደቡ አምባሳደሮች ምደባን አስመልክቶ ጠንክር ያሉ ጥያቄዎች በምሁራኑ ተነስተው የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አደም ፋራህ ከዩኒቨርሲቲው የስራ ሀላፊዎች ለተነሱ ሀገራዊ ጥያቄዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ እና ገለፃ አድርገዋል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ለዩኒቨርስቲው አመራሮች፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራን አሁን ላይ ካለው የኑሮ ውድነት ምክንያት በእጅጉ መፈተናቸውን ተከትሎ የመምህራንን የመኖሪያ ቤት እጥረትን ከመቅረፍ አንፃር ክልሉ በቀጣይ የቤት መስሪያ ቦታን ከማመቻቸት አንጻር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ከንቲባው ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ውስጥ ለሚታዩ የፀጥታ ችግሮች ወንጀለኞችን ተጠያቂ የሚያደርጉ ስራዎች ሲሰሩ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ፍትህን ለማረጋገጥ በሚደረጉ እነቅስቃሴዎች ላይ እንቅፋት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊደረግ የታሰበው የህገ-መንግስት ማሻሻያ ስራዎች እንዳሉ ሆነው የአማራ ክልልን ህገ-መንግስት እና የክልሉን ባንዲራ የማሻሻል ስራዎችን የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ አየሰራ መሆኑን ዶ/ር ድረስ ሳሕሉ በውይይት መድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ በሰላምና ጸጥታ፣ በአገረ-መንግሥት ግንባታ፣ በማኅበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ምክክር ተደርጎ የጋራ የመፍትሔ ሃሳቦችም ተነስተዋል። በተለይም ደግሞ  አገራዊ የምክክር መድረኩ የታለመለትን አገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ማስፈን እንዲችል እንዲሁም ጠንካራ ሀገራዊ መግባባትን ለማምጣት የሚረዳ ጠንካራ ሀሳብ  በማቅረብ ምሁራን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አቶ አደም ፋራህ አስገንዝበዋል።

ሀገሪቱ አሁን ላይ ካለችበት ችግር ተላቃ ወደ ፊት እንድትጓዝና ቀጣይ ለሚደረገው ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ መግባባት ለማምጣት ከምሁራን ጋር በሚደረገው ሀገራዊ ውይይቶች በእጅጉ አስፈላጊ በመሆናቸው መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ ላይ   የሚገኙ የመፍትሄ ሀሳቦችን ለመንግስት ለፖሊሲ ግብዓትነት ስለሚጠቅሙ ቀጣይ  ከመምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች ትኩረት ተሰጥቷቸው እንደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ`

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

TikTok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY