ለፋይናንስ እና ኦዲት ሰራተኞች የIBEX ስልጠና ተሰጠ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለፋይናንስ እና ኦዲት ሰራተኞች የIBEX ስልጠና ሰጠ

(ከታህሳስ 20-23/2015ዓ.ም) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ከሁሉም የዩኒቨርሲቲው ግቢዎች ለተውጣጡ 40 የፋይናንስ እና ማዕከላዊ ኦዲተር ሰራተኞች ከአዲስ አበባ ገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ በመጡ አሰልጣኞች በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ዲጅታል ቤተመጽሐፍት የIBEX ስልጠና ተሰጠ፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ለሰልጣኞች እንደተናገሩት የIBEX ስልጠና የሚባለው የተቀናጀ የበጀት እና የወጭ የፋይናንስ ስርዓት አስተዳደርን ስለማዘመን ነው፡፡ ስልጠናውን ለመስጠት የተፈለገበት ምክንያት  ዘመናዊና አዳዲስ የፋይናንስ አሰራሮች በሚመጡበት ጊዜ የፋይናንስ ሰራተኞች አዲሱን አሰራር በመላመድ ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ ለማስቻል ነው፡፡ በመሆኑም እያንዳንዷን የስልጠና ሂደት በትክክል በመከታተል በፋይናንስ ወጥ የሆነ ዕውቀት ኖሯችሁ በስራችሁ ውጤታማ እንድትሆኑ እንፈልጋለን ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

የIBEX project office ከፍተኛ የIT ኤክስፐርት አቶ ዮናስ ሰሎሞን የዚህ ስልጠና አስፈላጊነት የመንግስት ፋይናንስ ስርዓት በተደራጀና ዘመናዊ በሆነ መልኩ በጀት ከገባ በኋላ ሪፖርት ማድረግ ለማስቻል ነው ብለዋል፡፡ ለውጤቱም በየወሩ በጀት አጠቃቀማችን እንዴት እንደሆነ ለገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት የምናቀርብበትን ሶፍትዌር ለሰልጣኞች ማሰልጠንና ማሳወቅ ነው፡፡ ሰልጣኞችም ከስልጠናው /ሶፍትዌሩ ምንድን ነው የሚሰራው?/ የሚለውን ካወቁ በኋላ ቢሯቸው በመግባት በተግባር ሰርተው ሪፖርት በየወሩ እያቀረቡ እውቀታቸውን ማሳየት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የስልጠና ዳይሬክተሩ አቶ ወርቁ አበበ ለአራት ተከታታይ ቀናት የወሰዳችሁት የተቀናጀ የበጀት እና የወጭ አስተዳደር ስልጠና ለፋይናንስ ሰራተኞች እና ኦዲተሮች የሂሳብ አሰራርን በዘመናዊ መልኩ ስራዎቻችሁን ቀለል ለማድረግ ታስቦ የተሰጠ ነው ብለዋል፡፡  አያይዘውም የሂሳብ መዝገብ አያያዝን በቀላሉ ለመስራት የሚያግዛችሁ ዕውቀትን አግኝታችኋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በዚህም መሰረት በስልጠናው ላይ በዋናነት ከIBEX ውስጥ መሰረታዊ የሚባሉትን Budget preparation, Budget Adjustment and Budget control ሞጅሎች በተገቢው መንገድ የወሰዳችሁ በመሆኑ ስራችሁን ከምንጊዜውም በላይ በተሻለ መልኩ ለመስራት የሚያግዛችሁ በመሆኑ ተቋማችሁን በቅንነት እና በታማኝነት እንድታገለግሉ አሳስባለሁ በማለት የአደራ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ለሰልጣኞች የተዘጋጀላቸውን የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል፡፡

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ`

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

TikTok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY