ለጡረተኞች የምግብ እህል በስጦታ

ለጡረተኞች የምግብ እህል በስጦታ ተበረከተላቸው

[ጳጉሜ 04/2014 ዓ/ም፤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ] የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ በቆጋ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ቦታ ላይ ያመረተውን 130 ኩንታል እህል ከዩኒቨርሲቲው በተለያየ ጊዜ በጡረታ ለተገለሉና አነስተኛ ገቢ ላላቸው አቅመ ደካሞች በስጦታ አበርክቷል::

የኮሌጁ የድህረ ምረቃ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዲን ዶ/ር ተስፋየ መላክ እንደገለፁት በቆጋ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስፍራ አብላጫው  ስራ ለምርምርና የዘር ብዜትን ለማስፋፋት ሆኖ ከዚህ ዓላማ የተረፈው መሬት የሚያመርተው ምርት ለተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ማለትም ከአሁን በፊት ፍላጉት ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሽያጭ ማቅረባቸውንና ከ125 ኩንታል በላይ የሚሆን እህል በተለያየ ጊዜ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ተስፋየ በማስከተልም ዛሬ የተሰጠው 130 ኩንታል እህል 121 ኩንታል ስንዴ፣ 4 ኩንታል ጤፍ እና 5 ኩንታል የዳጉሳ ምርት ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ውሳኔ አሳርፈውበት በጡረታ ከተገለሉት ሰዎች መካከል አነስተኛ ገቢ ያላቸውና አቅመ ደካሞችን ለይቶ ስም ዝርዝራቸውን ለኮሌጁ በላከው መሰረት ለጡረተኞች የኮሌጁ ዲን ዶ/ር አሳምነው ጣሰው አስረክበዋል፡፡

ኮሌጁ እህሉን ሲያስረክብ ጡረተኞች እንዳይንገላቱ በማሰብ በዩኒቨርሲቲው ተሽከርካሪ እስከ ቤታቸው ድረስ በማጓጓዝ አኩሪ ተግባር አከናውኗል፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official

Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt

LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university

Twitter: - https://twitter.com/bdueduet

Tiktok:- https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL

website :- www.bdu.edu.et

#BDU60th_ANNIVERSARY