የሀዘን መግለጫ
BiT-BDU
24 Dec, 2025
ወጣት ዮርዳኖስ በ 2016 ዓ.ም በሶፍትዌር ምህንድስና 3.98 የማዕረግ ውጤት በልዩ ብቃት ትምህርቱን ከማጠናቀቅ አልፎ ራሱን በተለያዩ ስልጠናዎች በከፍተኛ ደረጃ እያበቃ ነበር። ከዚህም ባሻገር በተለያዩ የቴክኖሎጂ ሞያዎች አና ምርምሮች ላይ በከፍተኛ ደረጃ ለተለያዩ የውጭ እና ሃገር ውስጥ ተቋማት አስተዋጾ በማድረግ ላይ ነበር።
ጥቂቶቹን ለመዘርዘር፡ ሶፍትዌር ምህንድስና በMinab IT Solution PLC፣ ሰው ሰራሽ አስተው ሎት የቋንቋ ሞዴሎች ምርምር በLLMs፣ የኮምፕዩተር ትምህርት ይዘቶችን በማዘጋጀት በAfrica to Silicaon Valley፣ እንዲሁም አማርኛን ወደ ግዕዝ የሚቀይር ስርዐት፣የስራ አመልካቾች ማምልከቻ የሚያሰላስል ስርዓት፣ የመረጃ ጥንቅርን አስተዳደር ስርዓት ወዘተ በህይወት ጊዜው አበርክቶት በማድረግ የነበረ ወጣት ተመራማሪ ነበር።
ወጣት ዮርዳኖስ በትምህርት ቆይታው ተወዳጅና ትሁት እንደነበረ ጓደኞቹ ይመሰክሩለታል።
የኮምፕዩቲንግ ፋኩልቲ በወጣት ዮርዳኖስ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ለወዳጆቹ እና ቤተሰቦቹ ልባዊ መጽናናት ይመኛል።
ቀን 07/04/2018 ዓ.ም