የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በዩኒቨርስቲው እየተሰጠ ነው

Campus Name

30 Jun, 2025

የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በዩኒቨርስቲው እየተሰጠ ነው

8883 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በባሕርዳር ዩኒቨርስቲ እየተፈተኑ ነው። የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ እና በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበሪዊ ክላስተር አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ ተና ጣቢያዎች ተገኝተው የፈተናውን ሂደት በመመልከት ተፈታኞችን አበረታተዋል።

በዩኒቨርስቲው በኮምፒውተር እና በወረቀት በአጠቃላይ 8883 ተፈታኞች እንደሚፈተኑ ተገልጿል።

በፔዳ ግቢ ፣ ሰላም ግቢ እና በፖሊ በሶስት ግቢ የፈተና ጣቢያዎች ፈተናው እየተሰጠ ሲሆን በወረቀት የተፈጥሮ ሳይንስ በመጀመሪያው ዙር 2010 የሚፈተኑ ሲሆን በሁለተኛው ዙር በማህበራዊ ሳይንስ 2506 በድምሩ 4516 ተማሪዎች በሁለት ተከታታይ ዙሮች በወረቀት ይፈተናሉ።

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ፈተናውን ለሚወስዱ ተማሪዎች ለ50% እና በላይ ተፈታኞች በኮምፒተር ፈተናውን እየሰጠ ሲሆን በፔዳ ግቢ (ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ህንጻዎች) በተፈጥሮ ሳይንስ 2382 በማህበራዊ ሳይንስ 1985 ተማሪዎች በድምሩ 4367 ተማሪዎች ይፈተናሉ።