ለመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

Poly Campus

26 Sep, 2025

Event Content

ለመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
********
የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የመግቢያ መስፈርት መሰረት በመደበኛ መርሃ ግብር በግላቸው ከፍለው በመደበኛው መርሃግብር የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉና በግላችው ከፍለው መማር የሚፈልጉ አመልካቾች ከመስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚፈልጉትን የትምህርት ፕሮግራም (Department) በመምረጥ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የመግቢያ መስፈርት
✔️ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ፤
✔️ በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያላቸው፤
ለማመልከት የሚያስፈልጉ፣
✔️ የ12ኛ ክፍል ካርድ ወይም የአቅም ማሻሻያ ውጤት ዋናውንና ኮፒ
✔️ የማመልከቻ ክፍያ፤ 300.00 (ሶስት መቶ) ብር

የማመልከቻ ቦታ፤ 
✔️ ባሉበት ሆነው  በ”online” ድረ-ገጽ: https://studentportal.bdu.edu.et/OnlineApplication ገብተው ማመልከት ይችላሉ::
✔️  ወይም ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሬጅስትራርና አሉምናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመምጣት ማመልከት ይቻላል::

ማሳሰቢያ፡- 
✔️  ተማሪዎች የሚማሩት የትምህርት መስክ በመረጡት ይሆናል፡፡
✔️ በርካታ አመልካቾች ያሉባቸው ፕሮግራሞች በውድድር የሚለዩ ይሆናል።
✔️  በአቅም ማሻሻያ ውጤት ለሚገቡ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት (Official Transcript) ከምዝገባ በፊት ማስላክ ይኖርባቸዋል፡፡

studentportal.bdu.edu.et (https://studentportal.bdu.edu.et/OnlineApplication)
Bahir Dar University - Online Student Portal