ማስታወቂያ
ለክረምት ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በክረምት መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ እና በሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በግል ከፍለው ወይም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉና መስፈርቱን ለሚያሟሉ አመልካቾች ከሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን አመልካቾች የሚያመለክቱባቸውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር እና የመግቢያ መስፈርቶችን ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች፣
የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፤
ኦፊሻል ትራንስክርፕት
በመስሪያ ቤት ስፖንሰርነት ለሚያመለክቱ አመልካቾች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት የስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የ National Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ያለው/ያላት፣
ለማመልከቻ የተከፈለበት ደረሰኝ (Application fee 300 ብር)፣
photo
