የማህበራዊ ሳይንስ ፋካልቲ ለትምህርት ጉባዔዉ አባላት የአመራርነት ስልጠና አሰጠ፡

የማህበራዊ ሳይንስ ፋካልቲ ለፋካቲዉ የትምህርት ጉባዔ አባላት ለሶስት ተከታታይ ቀናት(ከግንቦት 25—27/2014 ዓ.ም) የአመራርነት ስልጠና አሰጠ፡፡ ስልጠናዉ የፋካልቲዉ አመራር ስለአመራራርነት ያላቸዉን  ግንዛቤ እንዲያጎለብቱ እና የአመረራር ክህሎታቸዉን እንዲያሳድጉ ያለመ  ነዉ፡፡ ስልጠናዉ በበጀት አመቱ እቅድ ተይዞለት በተያዘለት ጊዜ መሰጠቱም ታዉቋል፡፡

 ስልጠናዉ በሁለት ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን የመጀመሪያዉ ስልጠና ትኩረት ያደረገዉ ስለ አመራርነት ምንነት እና አንድ መሪ ምን አይነት ክህሎቶች ሊኖሩት እንደሚገባና ማስወገድ  ስለሚገባቸዉ ባህርያት በስፋት አቅርበዋል፡፡ የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮዊችን እና ልምዳቸዉን በማንሳት ለተሳታፊዎች ግንዛቤ ላማስጨበጥ ሞክረዋል፡፡ ከዚህም በተጫማሪ ተሳታፊዎች ሃሳባቸዉን እና ልምዳቸዉን እንዲያጋሩ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማሳንሳት ሰፊ የልምድ ልዉዉጥና ዉይይት እንዲካሄድ አድርገዋል፡፡

 ሁለተኛዉ ስልጠና ሰለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራርነት በስፋት ተንትነዋል፡፡ አሰልጣኙ የክፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ከሌሎችች ትምህርት ተቋማት አንጻር ምን ለዬት  እንዲሚያደርገዉ አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም አንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም አመራር ሊያዳብራቸወ ስለሚገቡና ሊያስወግዳቸዉ ስለሚገቡ ባህርያት በስፋት አቅርበዋል፡፡ በዚህም ረገድ በዪኒቨርሲቲያችን ያለዉን ተጨባጭ ሁኔታ እያነሱ ሰፊ ዉይይት ተካሂዷል፡፡ ሰልጣኞች ከስልጠናዉ ብዙ ልምድ እና እዉቀት እንዳገኙ እና ለወደፊት የስራ ስምሪታቸዉም እንደሚያግዛቸዉ ገልፀዋል፡፡  

 

Share