የሳይንስ ኢንኩቤሽን ማዕከል (STEM) ለተማሪዎች

የሳይንስ ኢንኩቤሽን ማዕከል (STEM) ለተማሪዎች ሲሰጥ የነበረውን የተግባር ተኮር ትምህርት አጠናቀቀ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ነሐሴ 30/2014 (ባዳዩ-BDU) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ኢንኩቤሽን ማዕከል /STEM/ በ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ-ግብር ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረውን የተግባር ተኮር ትምህርት አጠናቀቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሳይንስ ኢንኩቤሽን ማዕከል /STEM/ ከባሕር ዳር ከተማ ከሚገኙ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ-10ኛ ክፍል ከሚገኙ ተማሪዎች ውስጥ በመመልመል በክረምቱ መርሃ-ግብር የተግባር ተኮር ትምህርት ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ተማሪዎች ስልጠናቸውን በማጠናቀቃቸው ሽኝት አድርጎላቸዋል፡፡

በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምር/ማህ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራው ማዕከሉ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ መስኮች ከ3,090 በላይ ተማሪዎችን በማሰልጠን አስተዋፆ እያረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ተስፋዬ አክለውም ተማሪዎች የመማር ፍላጎታቸውን የሚጨምር መልካም ቆይታና ውጤታማ ጊዜ እንደነበራቸው አውስተው፣ የቀሰሙትን የፈጠራና የሳይንስ ግንዛቤ ለሌሎች በማካፈል የዩኒቨርሲቲው አምባሳደር እንዲሆኑ አደራ በመስጠት በክረምቱ የትምህርት ቆይታቸው ያካበቱትን ዕውቀት ወደ የት/ቤታቸው ሲመለሱ የተማሩትን ለሌሎች የክፍል ጓደኞቻቸው ማካፈል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የሳይንስ ኢንኩቤሽን ማዕከሉ ም/ዳይሬክተር ዶ/ር አለሙ ተስፋየ በክረምቱ መርሃ-ግብር በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና ሂሳብ ትምህርቶች ለተማሪዎቹ በተግባር የተደገፈ ስልጠና መሰጠቱን በመግለጽ ስልጠናው ተማሪዎቹ ለራሳቸውም ሆነ ለአካባቢው ማህበረሰብ ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራ እንዲሰሩና የፈጠራ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚረዳ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

በተግባር ተኮር የትምህር ስልጠናውን ከተካፈሉ ተማሪዎች ውስጥ አብላጫ ውጤት ላመጡት እውቅና የመስጠት ፕሮግራም በእለቱ ተካሂዷል፡፡ በማዕከሉ Science Shared Camp, Summer Camp, Girls’ Camp, Project Work, Weekends, Lab Works የተሰኙ ፕሮግራሞች የሚሰጡ መሆኑም ታውቋል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ-BDU

Description: 💦Description: 💦Description: 💦Description: 💧Description: 💦Description: 💦Description: 💧Description: 💦Description: 💦Description: 💦

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for Inviting, like, share & visiting BDU page!