ማስታወቂያ:- ለሁሉም መደበኛና የማታ ተማሪዎች በሙሉ
ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለሁሉም መደበኛና የማታ ተማሪዎች በሙሉ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የምዝገባ ጊዜ እንደሚከተለው መሆኑን ያሳውቃል፡፡
1ኛ በ2014 ዓ/ም አዲስ ገቢ የነበራችሁና በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምክንያት የጀመራችሁትን ሴሚስተር ያቋረጣችሁ ሪፖርት የምታደርጉት፤
- ለማታ ተማሪዎች ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ/ም፤
- ለመደበኛ ተማሪዎች ጥቅምት 21 እና 22 ቀን 2015 ዓ/ም ይሆናል፡፡
2ኛ ሌሎች ተማሪዎች (የ2015 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ጨምሮ) የመጀመሪያ ሴሚስተር ምዝገብ የሚደረገው፤
- ለመደበኛ ተማሪዎች ጥቅምት 21 እና 22 ቀን 2015 ዓ/ም፤
- ለማታ ተማሪዎች ጥቅምት 24 እና 25 ቀን 2015 ዓ/ም ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፤- የ2015 ዓ/ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ውጤት በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ እና የፌስቡክ ገጽ ስለምናሳውቅ እንድትከታተሉ እያሳሰብን የተመረጡ ለምዝገባ ሲመጡ የሚከተሉትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ዋናውን የትምህርት ማስረጃ፤
- የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (Sponsorship Letter) በመስሪያ ቤት ስፖንሰርነት ለሚማሩ ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት
- የቅበላ ደብዳቤ (Admission Letter) ከድህረ-ምረቃ ት/ቤት
- ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት የደረሰላቸው ብቻ፤
- ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ፤
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
Monday, October 24, 2022 (All day)