ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ
በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን፡-
1ኛ. በትምህርት ሚኒስቴር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች፤
2ኛ. በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም የገባችሁና ወደ Freshman Program መግቢያ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ፤
3ኛ. ዩኒቨርሲቲው ባወጣው የመንግስት ስኮላርሽፕ (ወጭ መጋራት ያለበት) የተመዘገባችሁ እና
4ኛ. በግላችሁ ከፍላችሁ በመደበኛው መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ድግሪ ለመማር ያመለከታችሁ በሙሉ፡
ስማችሁ ከ A እስክ Mengistu Asmamaw ያላችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በሰላም ግቢ እንዲሁም ስማችሁ ከ Mengistu Chekole እስከ Z ያላችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በፔዳ ግቢ
ሁሉም የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች ግሻ አባይ (ይባብ) ግቢ
የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 17-18 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡
ማሳሰቢያ፤
ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ፣
ብርድ ልብስ፤ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፤
የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፤
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፤
አራት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡
በተለያየ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ወሰነ ትምህርት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁ እና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ጥቅምት 20 እና 21 ቀን 2018 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም