Submitted by TANA on
ለሲኒማ እና ቴአትር ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመላ ሀገሪቱ በ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች ውስጥ በሲኒማና ቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል በቀጥታ ተቀብሎ በመደበኛው መርሐግብር ማስተማር ይፈልጋል፡፡
መስፈርቶች፡-
➫ ለጥበባት ልዩ ክህሎትና ተሰጥኦ ያለው/ያላት
➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ጀማሪ መርሐግብር ለመማር ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች
➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ወይም በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያለው/ያላት
✒️በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ ማኅበራዊ ሳይንስ ጀማሪ መርሐግብር ልትዛወሩ የምትችሉበት ሁኔታ ይመቻቻል ፡፡
የማመልከቻ ጊዜ
ከጥቅምት 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት
የምዝገባ ቦታ
ፔዳ ግቢ፣ የሲኒማና ቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ወይም ተከታዩን ሊንኩ ይጠቀሙ፦ https://forms.gle/KfHSF7QHUz2HBg5e7
ለበለጠ መረጃ፡-
0910479547 / 0928106018
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ!
ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ
photo