የአማራ ክልል ምክር ቤት እና በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋራ ለመሥራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

10 Sep, 2025

የአማራ ክልል ምክር ቤት እና በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋራ ለመሥራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ስምምነቱ በአቅም ግንባታ፣ በትምህርት፣ በጥናት ምርምር፣ በፕሮጀክት ቀረጻ እና ሌሎችንም ሥራዎች ዙሪያ በመደጋገፍ ለመሥራት መኾኑ ተገልጿል።
ስምምነቱን የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ሰብሳቢ ተወካይ መንገሻ አየነ (ዶ.ር) ናቸው የፈረሙት።

forem1fore2