ለሆስፒታሎች ድጋፍ ተደረገ

05 Nov, 2025

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ከ partner in education Ethiopia ጋር በመተባበር ለሁለት ሆስፒታሎች የዓይን ህክምና መስጠት የሚያስችል ሙሉ የዓይን ህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ ፡፡

በርክክብ ስነ ስርዓቱ የተገኙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተወልደ ውድነህ ዩኒቨርሲቲው የጉምሩክ ሂደትን ከማስፈፀም ባሻገር ሁሉንም የዓይን ህክምና መሳሪያዎች የቀረጥ ክፍያ ማለትም ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ እንደፈፀመ ገልፀውልናል ፡፡

የpartner in Education Ethiopia ተወካይ አቶ እዩኤል አማረ በበኩላቸው እርዳታውን ከ ISEE እና Rotary Club ማግኘታቸውን ገልፀው፤ ከባሕርዳር ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለሁለት ሆስፒታሎች ማለትም ለፍኖተ ሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የዓይን ህክምና መሳሪያዎች እንዲሁም ለቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግምታቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የዓይን ህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ መደረጉ ተገልፆል፡፡

imageimage