news

ለጸጥታና ደህንነት ሰራተኞችና ለፕሮክተሮች ስልጠና ተሰጠ

Campus Name

17 Mar, 2025

ለጸጥታና ደህንነት ሰራተኞችና ለፕሮክተሮች ስልጠና ተሰጠ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ ጸጥታና ደህንነት ዳይሬክቶሬትና ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር 80 ለሚሆኑ የጸጥታ ሰራተኞችና ፕሮክተሮች ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ከመጡ አሰልጣኞች አማካኝነት በደንበኞች አያያዝ ዙርያ አሁን እየተሰራ ካለዉ ነባራዊ ሁኔታና ቀጣይ በምን መልኩ ደንበኛን ማገልግል እንዳለባቸዉ በባለሙያዎች ከ4—7/10/2011 ለ4 ቀን በሁለት ዙር ስልጠና ተሰጧቸዋል፡፡ሰልጣኞችም ከሰልጠናዉ በቂ ዕዉቀት እንዳገኙና ቀጣይም ከዚህ በተሸለ መንገድ በሰለጠንነዉ አግባብ ደንበኞችን እንደምናረካ እርግጠኞች ነን በማለት አስተያየታቸዉን በመስጠት ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡