
ለፔዳ ግቢና ለቢዝነስና ኢኮኖሚክሰ ኮሌጅ አስተዳደር ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ
Campus Name
17 Mar, 2025
ለፔዳ ግቢና ለቢዝነስና ኢኮኖሚክሰ ኮሌጅ አስተዳደር ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከፔዳ ግቢ ማኔጅንግ ዳይሬክተርና ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ጋር በመተባበር በሁለቱም ግቢዎች በተዘጋጀዉ አዳራሽ ላይ በደንበኞች አያያዝና ስነምግባር ዙርያ ከቢዚነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በመጡ አሰልጣኞች ከ23-24/11/2011 ዓ/ም ድረስ ለ 110 ሰልጣኞች ስልጠና ተሰጧቸዋል፡፡ በዚህም ስልጠና ተሳታፊዎች ከስልጠናዉ ሰፊ ዕዉቀት እንዳገኙና ራሳችንንም እንድንፈትሽና እንድናይ ያደረገን በመሆኑ ለቀጣይ ስራችን ከፍተኛ መነሳሳትን ፈጥሮልናል ፡ነገር ግን በዚህ ስልጠና ላይ ሁሉም የዩንቨርሲቲዉ ማህበረሰብ በተለይ የበላይ አመራሮች ስልጠናዉን ቢወስዱ የተሸለ ስራ ይሰራል ብለን እናምናለን በማለት ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲዉ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኑት አቶ ወርቁ አበበ ይህ ስልጠና ለእናንተ ብቻ ሳይሆን ለዩኒቨርሲቲዉ ለሁሉም ማህበረሰብ በተከታታይነት የሚሰጥ ይሆናል ፡፡ ስለሆነም እናንተም በሰለጠናችሁበት አግባብ የደንበኛን ክቡርነት በመገንዘብ ከስልጠናዉ በቀ