bit

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(INSA) ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

Poly Campus

10 Oct, 2024

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(INSA) ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ   [ነሐሴ 04/2014፣ አዲስ አበባ- ኢስኮ/ባቴኢ] *************************************** በአዲስ አበባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መስሪያ ቤት ላይ በተካሄደው የፊርማ ስነስርዓት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን በመወከል የተገኙት የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት ከፊርማ ስነ-ስርዓቱ በሗላ ባደረጉት ንግግር INSA ተነሳሽነቱን ወስዶ መድረኩን ስላዘጋጀ ምስጋናቸውን አቅርበው ዩኒቨርሲቲወች ካላቸው ተልዕኮዎች አንጻር በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በቴክኖሎጅ ሽግግር መስክ ተስማርቶ ለሃገር ደህንነት በተለይም በሳይበር ሴኩሪቲ ዘርፍ መስራቱ የሚጠበቅ ቢሆንም ከINSA ጋር በመተባበር ሲሆን ደግሞ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ጠቁመዋል:: አክለውም የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ ፋይዳ የሚኖረው ወደ ተግባር ሲቀየር መሆኑን አውስተው ለዚህም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያለውን ቁርጠኝነት በመግለጽ በኢመደአ በኩልም ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንደሚጠብቁ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል:: የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰሎሞን ሶካ በበኩላቸው ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር እንዴት በጋራ በመስራት የሃገራችንን የሳይበር ጥቃት የመከላከል አቅም እንገነባለን? የዲጅታል ሉአላዊነታችንስ እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? በሚሉና መሰል ጉዳዮች ዙርያ ምክክር መካሄዱን ያነሱ ሲሆን ይህ የፊርማ ፕሮግራምም ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ መስራት ከምንም በላይ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት በዘርፉ  እምቅ አቅም ካላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም አብሮ መስራት እንዲቻል ታልሞ የተዘጋጀ መርሃግብር እንደሆነ አመላክተዋል:: የትብብር ሰነዱም በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የሰው ሃይል ግንባታን ማሳደግ፣ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰሩ ምርምሮችና ፕሮጀክቶች በሃገር ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ ማስቻል እና የታለንት ማዕከላት ልማትን ተጋግዞ ለመስራት የሚያስችሉ ስምምነቶችን ያካተተ እንደሆነ አስገንዝበው ተግባራዊ ለማድረግም ኢመድአ አበክሮ እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል:: የመግባቢያ ሰነድ መፈራረምን ተከትሎ ተቋማቱ በቀጣይነት ስለሚሰሯቸው የጋራ ተግባራት የባለሙያዎች የምክክር መድረክም በነገው እለት እንደሚካሄድ ይጠበቃል::   የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/bitpoly ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
bit

Bahir Dar University has signed memorandum of action with University of Gezira, Sudan

Poly Campus

09 Oct, 2024

Bahir Dar University has signed memorandum of action with University of Gezira, Sudan [July 30/2022, Bahir Dar - ISC/BiT] ***************************************************** Higher authorities from University of Gezira have already visited BiT to meet with the academic administration. The officials explored potential collaborations while visiting the institute for mutual benefit. They were able to tour the Seifu-BiT Makerspace as well as the laboratories of the faculties in the institute. The final agreement was signed by Dr. Firew Tegegne, President of Bahir Dar University, on behalf of BiT, and Vice Chancellor Sarah Eldin Mohamed on the behalf of University of Gezira. The memorandum of action is expected to benefit both parties, with academic quality serving as the cornerstone.   Information and Strategic Communication Directorate Facebook፡- https://www.facebook.com/bitpoly Telegram፡- https://t.me/bitpoly Website፡- https://bit.bdu.edu.et
bit

GiZ Private Sector Development in Ethiopia visited Seifu BiT Maker Space

Poly Campus

09 Oct, 2024

GiZ Private Sector Development in Ethiopia visited Seifu BiT Maker Space [July 29, 2022 Bahir Dar - ISC/BiT] ======================= GiZ Private Sector Development, one of the supporter of innovation ecosystem in Ethiopia including BiTec and the members from Dire Dewa, Adama Science and Technology, Wolaita Sodo, Jigjiga and Hawassa Universities visited Seifu BiT Maker Space. Dr. Amare Kassaw, BiTec Director, gave an overview about Seifu BiT Maker Space and what they are currently doing. He thanked former Scientific Director Dr. Seifu Admassu for his contributions to the makerspace and explained as if for recognizing that the makerspace had its current name. Dr. Amare clinched his briefing by reflecting on the visitors' questions and feedback. Giordano Dichter, Team Leader Innovation Ecosystem Expert as well as visitors from member universities, praised the work of the incubators at Seifu BiT Maker Space. Finally, Dr. Mekuanint Agegnehu, Deputy Scientific Director for Research & Community Service, delivered a speech to the visitors, where he attempted to explain the processes that Seifu BiT Makerspace has gone through as well as the challenges that they face. He concluded his speech by expressing how pleased the institute is with this incubation center and thanking the project's supporters and members on behalf of the institute. Information and Strategic Communication Directorate Facebook፡- https://www.facebook.com/bitpoly Telegram፡- https://t.me/bitpoly Website፡- https://bit.bdu.edu.et
bit

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2014 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ

Poly Campus

09 Oct, 2024

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ2014 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ [ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር - ኢስኮ/ባቴኢ] ========================= ኢንስቲትዩቱ ለ3 ተከታታይ ቀናት በጎንደር ከተማ ሲያካሂደው የነበረውን የሪፖርት ግምገማ መድረክ በትናንትናው ዕለት አጠናቅቋል፡፡ በመድረኩ ሁሉም ዲኖች፣ ዳይሬክተሮችና የማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊዎች የየክፍላቸውን አመታዊ የእቅድ ክንውን ሪፖርት በየተራ ያቀረቡ ሲሆን በክንውኖቹ ላይም አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርቦባቸው ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ በመጨረሻም የተቋሙ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረዴ በዛብህ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡  በመድረኩ የመክፈቻና የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት ያሳለፍነው የበጀት አመት እንደሃገርም እንደተቋምም ብዙ ፈተናወችና ውጣውረዶች የበዙበት ቢሆንም ሁሉም ክፍሎች ችግሮችን ተቋቁመው እቅዳቸውን ለማሳካት የሄዱበት ርቀት ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ ገልጸው ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ አክለውም የዚህ መድረክ ዋነኛ አላማ በክንውኑ የነበሩ ክፍተቶችን በጋራ የመለየትና ለቀጣይ የበጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ትምህርት ወስዶ ስኬታማ ክንውን ለመፈጸም ወሳኝ ግብዓት ማግኘት እንደነበር ጠቁመው ከዚህ አኳያም መድረኩ ግቡን ያሳካ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የውይይት መድረኮችን የአ/ም/ሳ/ዳይሬክተሩ ዶ/ር ደምሰው አልማው እና የም/ማ/አ/ም/ሳ/ዳይሬክተሩ ዶ/ር መኳንንት አገኘሁ እየተፈራረቁ የመሩ ሲሆን አጠቃላይ ፕሮግራሙን የተቋሙ ጠቅላላ የጥራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አስተባብሯል፡፡  Information and Strategic Communication Directorate Facebook፡- https://www.facebook.com/bitpoly Telegram፡- https://t.me/bitpoly Website፡- https://bit.bdu.edu.et
bit

BiT-CDC has successfully delivered a three-month training program called Full Stack Development Training in collaboration with MinabTech (HaHu Jobs) PLC.

Poly Campus

09 Oct, 2024

BiT-CDC has successfully delivered a three-month training program called Full Stack Development Training in collaboration with MinabTech (HaHu Jobs) PLC. [July 26, 2022 Bahir Dar - ISC/BiT] ======================== Industries have entered a new era of automation and digitization. This will have a significant impact on the skill demand of university students who need to remain competitive. Almost every job in the industry is changing, some quite dramatically, and new job creation must deal with new technological and digital skills. One of the defining business problems of our time is preparing graduate students for future employment. However, most universities do not address it in their formal education through their own curriculum. With this, BiT-CDC came up with Skill based training and competition program. One of the training is named Full Stack Development Training. It should be noted that an MOU was signed with MinabTech (HaHu Jobs) PLC. Following the orientation, 136 students were able to sign up for homework assignments. The company then sent trainers for three months to screened trainees in Back-end development, Front-end development, and Mobile app development. Initially, there were 50 trainees, but it was discovered that only 18 could complete it by the end of the week. The training covers single file components, components in depth, Reusability, Routing, Hands on Vue, npm package manager, CSS framework, setting up a tailwind, HTML and CSS recap, JavaScript design,  front end design, Hands on Figma, Router and local storage, GraphQL, single page apps, Vuejs and about Vue, Database and DBMS, characteristics of DBMS, database type, relational database, non-relational database, About Docker and Hasura, Dart programming, Introduction to Flutter, Setting up flutter SDK, Widgets, Network request, Data Persistence, State, Managing a state and state management tools.  According to Mr. Kaleab Mezgebu, Co-founder and operation manager, two trainees will be recruited and six of them will be given graduate internship opportunities.  On-campus recruitment will be active after the final exam. The training will conclude with great recognition by trainees for the glimpse experience and opportunities. Information and Strategic Communication Directorate Facebook፡- https://www.facebook.com/bitpoly Telegram፡- https://t.me/bitpoly Website፡- https://bit.bdu.edu.et
bit

በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል እና ምግብ ምሕንድስና ፋኩልቲ ያዘጋጀው ዓመታዊ ወርክሾፕ ተካሄደ

Poly Campus

09 Oct, 2024

በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል እና ምግብ ምሕንድስና ፋኩልቲ ያዘጋጀው ዓመታዊ ወርክሾፕ ተካሄደ [ሐምሌ 16/2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር - ኢስኮ/ባቴኢ] ========================= በወርክሾፑ መግቢያ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት እንደገለጹት የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትስስር ወሳኝ ከመሆኑ ባለፈ ተማሪዎችን ብቁ ኢንተርንሺፕ ቆይታ እንዲኖራቸው ያደርጋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመት ቢሮ ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው  ያደጉት ሐገራት ደሀ የሚባሉት ሀገራትን ሐብት ለመቀራመት ጥረት እንደሚያደርጉ ጥቁመው የክልሉ መንግስት የኢንዱስትሪ መንደሮችን ገንብቶ ለባለሐብቶች ከመስጠት ባለፈ ብድር በማመቻቸት ኢንዱስትሪው ኢንዲሻሻል ጥረት ያደርጋል። በዚህም የእውቀት ሽግግር እንዲኖር ማድረግ እና የውጪ ምንዛሬ አቅምን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።  በሌላ በኩል የዩኒቨርሲቲው አልሙናይ ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው የኬሚካል እና የምግብ ኢንዱስትሪዎች ሀገር ከመቀየር ባለፈ ለሌሎች ኢንዱስትሪዎች ግብዓት እንደሚሆኑ ጠቅሰው ኢንዱስትሪዎች እና ዩኒቨርሲቲዎች በተለያየ መንገድ ውስጥ እየተጓዙ በመሆናቸው ማደግ አዳጋች መሆኑን ገልጸዋል። ይህንን በማስመልከት የፋኩልቲው ዲን ዶ/ር መታደል ካሳሁን የፋኩልቲውን አቅም ብሎም በውስጡ የተሰሩ ሥራዎችን ገልፀው ምርምሮችን እና የተማሪዎችን ዓቅም ማጎልበት ላይ እንደሚሰራ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አድጀንት ፕሮፈሰር ለሊሳ ዳባ የሕዝብ ቁጥር መጨመር አሳሳቢ እንደመሆኑ መጠን እና የወደፊቱ ሕዝብ በብዙ መጨመር በምግብ ራስን የመቻል ስራዎች ላይ አደጋ ደቅኗል። በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ እንደነበረ ገልፀው የኮቪድ መምጣት ኢትዮጵያን ጨምሮ ዓለምን ወደኋላ የጎተተ እንደሆነ ገልፀዋል። በኢንዱስትሪ ሚንስቴር የኬሚካል እና ኮንስትራክሽን እቃዎች ጥናት ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክተር ወ/ሮ ነጻነት አበበ እንደተናገሩት የሚሰሩበት ክፍል በ70ቹ የነበረው ጥንካሬ ከጥቂት ለውጦች በዘለለ የሚጠበቀውን ያህል አለማደጉ አሳሳቢ እንደሆነ ሁሉ ኢንዱስትሪዎች እንዲያድጉ ሰላም እና የተሳለጠ ቢሮክራሲ የሚያስፈልግ ሆኖ በተናጠል ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ይልቅ መንግስት በሕብረት ለሚከናውኑ ሥራዎች ትኩረት እና ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። ይህም ሚንስቴሩ ደሴት  ሆኖ የሚተገብረው ሳይሆን ከኢዱስትሪዎች እና ትምሕርት ተቋማት ጋር መተባበር መሆኑን ገልፀዋል። በትምሕርት ሚንስቴር የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ስልጠና ምርምር እና ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ዳንኤል በበኩላቸው ኢንዱስትሪዎች የሚያመርቷቸውን ምርቶች ጥራት እና ብዛት ከማሳደግ አንጻር እዚህ ግባ ይሚባል ምርምር ካለመሰራቱ ባለፈ ከትምሕርት ተቋማት ጋር ያላቸው ትስስር ደካማ መሆኑ አሳሳቢ መሆኑን ገልፀው ገንዘብ እና የአቅም ውስንነት አስቸጋሪ በሆኑበት ሁኔታ ውስጥ የኢንዱስትሪው ውድድር መድረክ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራስን መቻል አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።  በእለቱ የተለያዩ ሓሳቦች የተሰነዘሩ እና ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን ሁሉም የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ስምምነት ተደርሷል። በመዝጊያው ወቅት የኢንስቲትዩቱ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት አገኘሁ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ምርምር እና እድገት የማይነጣጠሉ መሆናቸውን ጠቁመው ኢንስቲትዩቱ ያለውን እምቅ ኃይል እና አቅም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ለመስራት የሚያስችለው መሆኑን በመግለጽ በጋራ ሆኖ በትንሹ በመጀመር ወደላቅ ደረጃ መምጣት እንድሚቻል ጠቁመዋል።  Information and Strategic Communication Directorate Facebook፡- https://www.facebook.com/bitpoly Telegram፡- https://t.me/bitpoly Website፡- https://bit.bdu.edu.et