bit

የዘላቂ ኃይል ልማት ለገጠር ሥራ ፈጥራ ፕሮጀችት ምረቃ በዳንግላ ወረዳ ዳንጊሽታ ቀበሌ ተካሄደ

Poly Campus

09 Oct, 2024

የዘላቂ ኃይል ልማት ለገጠር ሥራ ፈጥራ ፕሮጀችት ምረቃ በዳንግላ ወረዳ ዳንጊሽታ ቀበሌ ተካሄደ በጀርመኑ Technical University of Munich በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በትብብር የተገነባው በታዳሽ ኃይል የመስኖ ልማት እና ኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ሥራ መጀመሩን አስመልክቶ  የፕሮጀክቱ ምረቃ ተካሄደ። በፕሮግራሙ መክፈቻ ወቅት የፕሮጀክቱ መሪ ዶ/ር ንጉስ ጋብየ እደተናገሩት ዘመናዊ እና ታዳሽ  ኃይል ከማመንጨት ባለፈ ወጣቶችን በትናንሽ የማኑፋክቸሪንግ ሥራ ዘርፍ እንዲሰማሩ እድል ይፍጥራል። እንደ እሳቸው ገለጻ 160 ሜትር ጥልቅ ጉድጓድ ተቆፍሮ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ ፓምፕ ተግጥሞለት ለመስኖ ግልጋሎት ውሏል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ለአርሶ አደሮች አጭር ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን በጠብታ መስኖ እስከ 10 ሄክታር  መሬትን ማልማት የሚችል እና 1800 አባውራዎችን የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ያደርጋል። ለዚህም ሥራ የሚሆን ገንዘብ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 4 ሚሊዮን ብር የተለገሰ ሲሆን ወጣቶችን አደራጅቶ ወደ ሥራ ከመሰማራት ባለፈ ምርምር ለሚያደርጉ የድሕረ መረቃ ተማሪዎች እንደ Living Lab ሆኖ የሚያገልገግል ስፍራ ነው። በእለቱ የተገኙት የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ የቀበሌው ነዋሪዎችን እና ባለ ድርሻ አካላትን አመስግነው  ሥራው ከ2007 ዓም ጀመሮ በምርምር ሂደት ላይ እንደነበር ብሎም ከ15 የሚበልጡ የድሕረ ምረቃ ተማሪዎች እድሉን እንዳገኙ ገልጸዋል። የሲቪል እና ውሐ ሐብት ምህንድስና መምሕር እና የፕሮጀክቱ ተሳታፊ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ በበኩልቸው የሕብረተሰቡን ቁርጠኝነት አድንቀው በአሁኑ ወቅት 10000ሊትር የሚይዝ የውሃ ታንከር ተተክሎ ለሕበረተሰቡ ንፁህ የባንቧ ውሃ በተመረጡ ቦታዎች መቀመጡን ገልጸው አርሶ አደሮችን ትጋት አድንቀዋል።  የቀበሌው ነዋሪ እና በህልውናው ጦርነት ተሳታፊ የነበሩት ሚሊሻ ውባንተ እያሱ የዶ/ር ንጉስ ጋብዬን ሐሳብ በመጋራት ለወጣቶች የጸጉር ቤት ሥራ ጀመሮ እንጨት መሠንጠቂያ ቤቶችን ለመሥራት በዕቅድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። እንደ ሚሊሻ ውባንተ ንግግር በአሁኑ ወቅት 28 አባውራዎች የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ሆነው የመስኖ ድንች ያለሙ ሲሆን በቀጣይ ሌሎች ለመቀላቀል በሂደት ላይ መሆናቸውን ለማየት ተችሏል። በዚህ ወቅት ካነጋገርናቸው አርሶአደሮች ውስጥ ጥቂቶቹ የባሕር ዛፍ ደኖቻቸውን በመመንጠር ላይ መሆናቸውን ገልጸው በ 5 ዓመት የሚያገኙት የባሕር ዛፍ ትርፍ ከመስኖው ዝቅተኛ መሆኑን በመግለጽ ወደ መስኖው ለመግባት በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።  በኣጠቃላይ በፀሐይ ኃይል ይሚሰራው ታዳሽ ኃይል እስከ 25 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጨ ሲሆን 30ሊትር በሰከንድ የሚሆን ውሃ ከጉድጓዶቹ መውጣት መቻሉን ዩኒቨርሲቲው መምህር እና የፕሮጀክቱ ተሳታፊ አቶ ነገሰ ያዩ ገልጸዋል። ቁፋሮው በአማራ ውሓ ስራዎች የተከናወነ መሆኑን በመጠቆም የአማራ ክልል ውሐ እና ኢነርጂ ቢሮ ጥናት በማካሄድ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳበረከተ አቶ ነገሰ ገልጸዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ገደፋው አላግባብ ብክነት እና ጥፋት እንዳይኖር መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸው በሞዴል ደረጃ የሆንው ስራውን በማስፋፋት ወደሌሎች ቦታዎች ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል። በሌላ በኩል ለመዝረፍ የሚፈልጉ ኃይሎች እንደመኖራቸው መጠን ቀን ከለሊት ክትትል እንደሚያስፈልገው በገልጻቸው ወቅት አብራርተዋል። በተጨማሪም የአዊ ዞን፣ የዳንግላ ወረዳ እና የዳንግሽታ ቀበሌ አመራሮች በየደረጃቸው አስተያየታቸውን ገልጸዋል።  በመጨረሻም ለፕሮጀክቱ እዚህ መድረስ ከፍትኛ ሚና ነበራቸው የተባሉ ግለሰቦችን እውቅና የመስጠት መርህ ግብር ተካሂዶ  የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል።   የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/bitpoly  ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
bit

Bahir Dar University, Bahir Dar City Adminstration and G.A. Engineering Associates P.C. have signed a comprehensive memorandum of understanding.

Campus Name

09 Oct, 2024

Bahir Dar University, Bahir Dar City Adminstration and G.A. Engineering Associates P.C. have signed a comprehensive memorandum of understanding. The profound collaboration has been signed to promote and fulfill the construction of the Municipal Solid Waste Production (MSW) Energy.  The agreement will account for MSW Energy's design, construction, and production, which will be funded by Trilogy Financial Group Inc.  The group will provide electricity, renewable fuel, and natural gas to the city of Bahir Dar.  On the other hand, G.A. Engineering Associates P.C. led by one of our alumni Engineer Girma Allaro will provide agreements and enable the implementation of the Bahir Dar MSW Energy industry by and between Bahir Dar Municipality, Bahir Dar University, and Trilogy Financial Group Inc. Information and Strategic Communication Directorate Facebook፡- https://www.facebook.com/bitpoly Telegram፡- https://t.me/bitpoly Website፡- https://bit.bdu.edu.et
bit

የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

Poly Campus

09 Oct, 2024

የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ [ሚያዝያ 10/2014 ዓ.ም፣ ባህር ዳር - ኢስኮ/ባቴኢ] በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት እና ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ ኢንዱስትሪዎችን ከማገዝ አንጻር በጋራ ለመሥራት ያለመ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ የም/ማ/አ/ም/ሳ/ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት አገኘሁ እና የኮሌጁ ዲን አቶ አስጨንቅ ካሳ ተቋማቱን ወክለው ተፈራርመዋል፡፡ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ዶ/ር መኳንንት እንዳሉት የትምህርት ተቋማቱ ወደ ኢንዱስትሪው ከመሄድ ባሻገር ተማሪዎችን በሥራ ክህሎት እና የፈጠራ ሙያ ከማብቃት ጀመሮ ማሕበረሰብ ተኮር ሥራ ለመስራት ኢንዱስትሪዎች የሚገጥሟቸውን እክሎች እና ችግሮች ወደ ተቋማቱ በማምጣት አብረው መሥራት ተመራጭ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ አቶ አስጨንቅ ካሳ በበኩላቸው ኮሌጁ ተግባር ተኮር ትምሕርቶችን ከማስተማር ባለፈ የቡሬ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ጋር እየሠራ መሆኑን ጠቁመው ከባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር ሲሠራ የነበረውን ፕሮጀክቶች ወደላቀ ደረጃ እንዲመጣ ለማድረግ እና ኢንዱስቲሪያል ፓርኮቹን በጋራ ለማገዝ ስምምነቱ ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ኮሌጁን ወክለው የተገኙት ዶ/ር ዋለ ፍሬው በበኩላቸው ኮሌጃቸው ከዚህ በፊት Job Fair ማካሄዱን ጠቁመው የተሻለ ሲኬት እንዲመጣ የጋራ ተጠቃሚነትን መርህ ያደረገ ስምምነት መፈፀሙን አወድሰዋል። ይህም ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰው ኃይል ከማሟላት አንጻር ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ያደርጋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ታሕሳስ መጨረሻ ያዘጋጁትን የ Job Fair ሪፖርት ለባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ያቀረቡ ሲሆን ተማሪዎችን ከማብቃት አንጻር CDC ጋር ለመሥራትም ሃሳብ እንዳላቸው ከገለጻው መልስ በነበረው የውይይት ወቅት ተጠቁሟል። የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ፌስቡክ፡- www.facebook.com/bitpoly ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et

Paragraph

Submitted by admin on

Paragraph

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Donec molestie luctus condimentum. Curabitur cursus quam eget tincidunt pellentesque. Vestibulum sit amet condimentum ipsum, non porta tellus. Maecenas mollis cursus ipsum. Ut velit dolor, tincidunt a euismod id, imperdiet eu lacus. Nam felis magna, faucibus ac tristique a, varius et mi.

highlights

Submitted by admin on

Highlights

Vestibulum tempus, augue ut posuere accumsan, magna nulla rhoncus ligula, nec convallis mi justo sed tellus. Cras commodo accumsan sapien, nec aliquam purus finibus vel. Phasellus in sapien id quam varius facilisis eu ac nulla. Donec eget magna id tortor odales interdum vel sit amet tellus.

Text Formats

Submitted by admin on

Text Formats

H1 Heading

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Donec molestie luctus condimentum. Curabitur cursus quam eget tincidunt pellentesque. Vestibulum sit amet condimentum ipsum, non porta tellus. Maecenas mollis cursus ipsum. Ut velit dolor, tincidunt a euismod id, imperdiet eu lacus. Nam felis magna, faucibus ac tristique a, varius et mi.Sed volutpat turpis non nisl commodo blandit ac quis elit.