Academic Calendar

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ አገልግሎቶችና አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች (Service Standards)

 

ተ.ቁ

የሚሰጡ አገልግሎቶች

አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

የሚወስደው ጊዜ

1

የትምሕርት ማስረጃ ላይ የሆህያት ግድፈትን ማስተካከል Spelling Error Committed by the Student

የተሳሳተውን ዶክመንት በአካል ይዞ በመቅረብ የማስተካከያ ፎርም መሙላትና የተቀመጠውን ክፍያ መፈጸም (ክፍያ 50 ብር)

10 ደቂቃ

2

የትምህርት ማስረጃ ኮፒ አገልግሎት

·         1996 ዓ.ም ጀምሮ በቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም የተመረቁ ከሆነ የወጭ መጋራት የከፈለበትን ማስረጃና ደረሰኝ ማቅረብ የሚጠበቅ ሲሆን የወጭ መጋራት ውል ኮፒ ግን በማንኛውም ወቅት መውሰድ ይቻላል፡፡

·         ከላይ ከተጠቀሰው ውጭ የሚሰጡ ተገልጋዩች የወጭ መጋራት ጥያቄ ሳይኖርባቸው ይስተናገዳሉ፡፡  (ክፍያ ለአንድ የትምህርት ማስረጃ 30 ብር)

10 ደቂቃ

3

የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ /Authentication)

·         ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም የተመረቁ ከሆነ የወጭ መጋራት የተከፈለበት ማስረጃና ደረሰኝ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ሌሎች ተገልጋዬች የትምህርት ማስረጃውን በአካል ይዞ በመቅረብ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ፡፡ (ክፍያ ለአንድ የትምህርት ማስረጃ 50 ብር)

15 ደቂቃ

4

ኦፊሺያል ትራንስክርቢት ለማስላክ ለሀገር ውስጥ

·         ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም የተመረቁ ከሆነ የወጭ መጋራት የተከፈለበት ማስረጃና ደረሰኝ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ሌሎች ተገልጋዬች ተዘጋጅቶ በቀረበው መጠየቅ ላይ የሚጠየቁትን መሰረታዊ መረጃዎች በትክክል በመሙላት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡ (ክፍያ ለአንድ የትምህርት ማስረጃ 60 ብር)

30 ደቂቃ

5

ኦፊሺያል ትራንስክርቢት ለማስላክ ለውጭ ሀገር

·         ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም የተመረቁ ከሆነ የወጭ መጋራት የተከፈለበትን ማስረጃና ደረሰኝ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ሌሎች ተገልጋዮች ተዘጋጅቶ በቀረበው መጠይቅ ላይ የሚጠየቁትን መሰረታዊ መረጃዎችን በትክክል በመሙላት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡ (ክፍያ ለአንድ የትምህርት ማስረጃ 100 ብር)

30 ደቂቃ

6

የስም ለውጥ በመማር ላይ ላሉ ተማሪዎች

·         በፍርድ ቤት የተረጋገጠ የስም ለውጥ ማስረጃ በማቅረብ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ (ክፍያ 100 ብር)

10 ደቂቃ

7

የትምህርት ማስረጃ ትክ /Document Replacement/ ኦርጅናል ጊዜያዊ ዲፕሎማ እና ስቱደንት ኮፒ (ለጠፋበት የት/ት መረጃ)

·         በህግ እውቅና ካለው አካል ስለማስረጃው መጥፋት ደብዳቤ ማቅረብ (ማስመዝገብ ወይም ሁኔታ መሞላቱን የሚገልፅ ሳይሆን ስለትምህርት ማስረጃ መጥፋት የሚያረጋግጥ መሆን ይጠበቅበታል)

(ክፍያ ለጊዜያዊ/ኦርጅናል የትምህርት ማስረጃ 100 ብር እና ስቱደንት ኮፒ 30 ብር)

30 ደቂቃ

8

የተለያዩ አካዳሚክ ቅፆችን መሙላት

·         በማስረጃው ባለቤት ሲጠየቅ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም የተመረቁ ከሆነ የወጭ መጋራት የተከፈለበትን ማስረጃና ደረሰኝ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን በሌሎች አረጋጋጭ አካላት ማስረጃው ሲጠየቅ ሊገለጽላቸው የሚፈለጓቸውን መረጃዎች በዝርዝር በመላክ አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል፡፡ (ክፍያ 50 ብር)

10 ደቂቃ

9

የልደት ዘመን (Date of Birth) ለውጥ

·         የልደት ሰርተፍኬት የመስጠት ስልጣን ከተሰጠው አካል የተረጋገጠ የልደት ሰርተፍኬት ፡፡ (ክፍያ 30 ብር )

5 ደቂቃ

10

የኮርስ ዝርዝር (Course Break Down)

·         ለተመራቂው /በተማሪው ጥያቄ መሠረት አገልግሎት ማግኘት ይቻላል፡፡ (ክፍያ 100 ብር)

30 ደቂቃ

11

ለሚመለከተው ሁሉ (To Whom it May Concern Letter)

·         ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም የተመረቁ /ላቋረጡ ከሆነ የወጭ መጋራት የተከፈለበት ማስረጃና ደረሰኝ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ሌሎች ተገልጋዬች ተዘጋጅቶ በቀረበው መጠይቅ ላይ የሚጠይቁትን መሰረታዊ መረጃዎች በትክክል በመሙላት አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ፡፡ ይሁን እንጅ በቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ሲማሩ ቆይተው ትምህርቱን ሲሰናበቱ አገልግሎቱን ከክፍያ ነጻ ይስተናገዳሉ፡፡ (ክፍያ ለአንድ የትምህርት ማስረጃ 30 ብር)

10 ደቂቃ

12

መማሪያ ቋንቋን የሚገልፅ ደብዳቤ (Medium of Instruction )

·         ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም የተመረቁ/ላቋረጡ ከሆነ የወጭ መጋራት የተከፈለበትን ማስረጃና ደረሰኝ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ሌሎች ተገልጋዬች በአካል ቀርበው በማመልከቻ በማቅረብ አገልግሎት ማቅረብ ይቻላል ፡፡ (ክፍያ 30 ብር)

30 ደቂቃ

13

መታወቂያ ካርድ ሲጠፋ መመማር ላይ ላሉ ተማሪዎች አገልግሎቱ በየኮሌጁ የሚሰጥ ነው   

·         ከፍርድ ቤት መጥፋቱን ማረጋገጫ ማምጣት

·         ከሬጅስትራር የመታወቂያ ካርድ ማሰሪያ (ID Replacement) ፎርም መውሰድ

·         በመጨረሻ የ30 ብር የተከፈለበት ደረሰኝ እና አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ  

10-15 ደቂቃ

14

ኦርጅናል ዲፕሎማ /Original Diploma/ ለመውሰድ

·         ከዚህ በፊት መደበኛ ተማሪ ከነበሩ የወጭ መጋራት የከፈሉበት ደብዳቤ ላይ ዋናው ሬጅስትራር ቢሮ በሚገኘው የወጭ መጋራት ቢሮ ስለ ትክክለኝነቱ እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡

·         ትምህርት ጨርሰው ከግቢው ሲወጡ (Clearance) የጨረሱበት ወረቀት /ለመደበኛ ፣ለማታ ፣ለክረምት፣ተማሪዎች በሙሉ የሚያገለግል/

·         ለሰው ተወክለው የሚመጡ ከሆነ የፍርድ ቤት ውክልና ያስፈልጋል፡፡

15-20 ደቂቃ

15

ዋናውን ኦርጅናል ማዘጋጃ ፎርም ለመሙላት (Diploma Preparation)

·         ከከፍተኛ የተማሪዎች ቅበላ ባለሙያ ቢሮ በመሔድ ፎርምና የክፍያ መጠን ማረጋገጫ መውሰድ

·         ፎርሙን በጥንቃቄ መሙላት ሁሉንም ፊደሎች (Capital Letter)መጠቀምን እና ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ

20-25 ደቂቃ

16

በድህረ ምረቃና በቅድመ ምረቃ በተከታታይና በርቀት  መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያመለክቱ

ለመጀመሪያ ዲግሪ

·         ዋናውን መረጃቸውንና ፎቶ ኮፒ ማምጣት፣ የበፊቱ ዲፕሎማ ወይም ደረጃ IV (Level 4)  የጨረሱ ከሆነ Official Transcript ከተማሩበት ተቋም ማስላክ፣

·         የደረጃ IV (Level 4) ከምዘና ማረጋገጫ (COC) ያለፈበትን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ፡፡

ሁለተኛ ዲግሪ

·         ዋናውን መረጃቸውንና ፎቶ ኮፒ ማምጣት፣

·         Official Transcript ከተማሩበት ተቋም ከምዝገባ በፊት መድረስ ይኖርበታል

15-20 ደቂቃ

 

ማሳሰቢያ፡- በተጠቀሰው የጊዜ መጠን የሚስተናገዱ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስገልጉ መስፈርቶችን ይዘው ሲገኙ ብቻ ነው፡፡