You are here

የጥሪ ማስታወቂያ

                                                                                                                                                            የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም

                                                                                የጥሪ ማስታወቂያ

                  በ2015 ዓ/ም በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ

በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር መስፈርት መሠረት በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ፤

  • ስማችሁ ከ”A — M” የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በዘንዘልማ ካምፓስ፤
  • ሁሉም የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) ተማሪዎች እና ስማችሁ ከ”N — Z” የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ተማሪዎች በግሽ አባይ (ይባብ) ካምፓስ፤

ከየካቲት 20 - 22 ቀን 2015 ዓ/ም ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲውን ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፤

1ኛ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ፣

  • ብርድ ልብስና አንሶላ፣
  • የስፖርት ትጥቅ፤
  • የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
  • 4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡

2ኛ በተለያየ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ወሰነ ትምህርት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ እና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በ2015 ዓ.ም 1ኛ ወሰነ ትምህርት ለመልሶ ቅበላ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን 1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ያቋረጣችሁ ግን መልሶ ቅበላ የምትጠይቁት በ2ኛው ወሰነ ትምህርት መሆኑን እናሳስባለን፡፡

3ኛ ከተገለጸው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት

Contact

 

 Main Registrar Office 

Tel:   0582205934

 

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2019- Bahir Dar University