መጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም
ለትምህርት ፈላጊዎች በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ
ለመጀመሪያ ዲግሪ እና PGDT ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በማታ (Extension) እና በርቀት (Distance) ፕሮግራሞች በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በPGDT ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ከመጋቢት 07 አስከ መጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ የምዝገባ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የመመዝገቢያ ጊዜውን ለተወሰኑ ቀናት ማራዘም በማስፈለጉ መማር የምትፈልጉ እና ከዚህ በፊት በማስታወቂያው የተገለጹ መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ የተራዘመ ስለሆነ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን የምታመለክቱባቸውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር ከዩንቨርስቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
Main Registrar Office
Tel: 0582205934
Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2019- Bahir Dar University