You are here

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

                                                                                                                                                ጥር 03 ቀን 2016 ዓ.ም

                                                                   ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው ወይም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉ

1ኛ በመደበኛው መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾችን፤

2ኛ በማታው መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ፤ የ2ኛ ዲግሪ አና የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም አመልካቾችን፤

3ኛ በርቀት መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ እና PGDT ፕሮግራም አመልካቾችን፤

ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 19 ቀን 2016 / ድረስ ለርቀት ፕሮግራም አመልካቾች በርቀት ማዕከላት፤ ለመደበኛና የማታ ፕሮግራም አመልካቾች ደግሞ ትምህርቱ በሚሰጥበት የአካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራር ጽ/ቤት ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለምዝገባ መሟላት የሚገባቸው፤

  • ለ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (Graduate Admission Test /GAT/) ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ፤
  • ለመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለመግባት በትምህርት ሚኒስቴር የወጣውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መስፈርት ወይም መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ፤
  • ለPGDT አመልካቾች በመምህርነት ሙያ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፤
  • ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም አመልካቾች በ2016 ዓ/ም ፕሮግራሙን ለመከታተል እድሉ ለተሰጣቸው በትምህርት ሚኒስቴር የወጣውን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፤

  • ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ማስላክ ይኖርባቸዋል (ለሚመለከታቸው ብቻ)፡፡
  • የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ገቢ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000224663378 መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
  • የተመረጡ አመልካቾች ዝርዝር ጥር 27 ቀን 2016 ዓ/ም የሚገለጽ ይሆናል፡፡ የመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት ምዝገባ ከጥር 30 እስከ የካቲት 02 ቀን 2016 ዓ/ም ይካሄዳል፡፡
  • በቂ የተማሪ ቁጥር የማያመለክትባቸው የትምህርት መስኮች አይከፈቱም፡፡

 

                                                             የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

                                       ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት

Contact

 

 Main Registrar Office 

Tel:   0582205934

 

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2019- Bahir Dar University