You are here

ለመጀመሪያ ዲግሪ እና PGDT ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

                                                                                                                                            መጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም

                                                                     ማስታወቂያ

                                         ለመጀመሪያ ዲግሪ እና PGDT ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የመግቢያ መስፈርት መሰረት በማታ (Extension) እና በርቀት (Distance) በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በPGDT ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም መስፈርቶችን የምታሟሉና መማር የምትፈልጉ አመልካቾች ከመጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ መጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን የምታመለክቱባቸውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር ከዩንቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የማመልከቻ መስፈርት፤ በትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት መሰረት

1ኛ በመሰናዶ ፈተና ውጤት ለሚያመለክቱ

  • በ2014 ዓ/ም በመጀመሪያ ዙር ለተፈተኑ ለተፈጥሮ ሳይንስ 300፤ ለማህበራዊ ሳይንስ 250፤ለዓይነስውራን ተፈታኞች 200 እና ከዚያ በላይ፤ በሁለተኛ ዙር ለተፈተኑ ለተፈጥሮ ሳይንስ 350፤ ለማህበራዊ ሳይንስ 300 እና ከዚያ በላይ፤ ለዓይነስውራን ተፈታኞች 250 እና ከዚያ በላይ፤
  • በ2013 ዓ/ም ለወንድ 330 ለሴት 320 እና ከዚያ በላይ፤
  • በ2012 ዓ/ም 140 እና ከዚያ በላይ (English, maths, Aptitude, physics/Geography) ፤
  • ከ2009 - 2011 ዓ/ም 295 እና ከዚያ በላይ፤
  • በ2008 ዓ/ም 275 እና ከዚያ በላይ፤
  • ከ2003 - 2007 ዓ/ም 265 እና ከዚያ በላይ፤
  • ከ1995 - 2002 ዓ/ም የመሰናዶ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢየ ውጤት ያስመዘገቡ፤

 2ኛ በዲፕሎማ ለሚያመለክቱ

  • ከ1994 ዓ/ም በፊት ዲኘሎማ ያጠናቀቁ፤
  • ከ1994 ዓ/ም በፊት ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በዲኘሎማ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ እና ከ1994 ዓ/ም በኋላ ከየትኛውም ተቋም ትምህርታቸውን በደረጃ-4 ያጠናቀቁ እና ደረጃ-4 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚያቀርቡ፤

 3ኛ ለPGDT በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፤

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች

  • የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ፎቶ ኮፒ፤
  • የብቃት ማረጋጫ (COC) (ለሚያስፈልጋቸው ብቻ)፣
  • ኦፊሻል ትራንስክርፒት (ለሚያስፈልጋቸው ብቻ)፣
  • ለማመልከቻ የተከፈለበት ሁለት ኦሪጅናልና አንድ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ደረሰኝ (ለርቀት ትምህርት 150 እና ለማታ 100 ብር)፣

የማመልከቻ ቦታ፤

  • ለማታ ትምህርት ፕሮግራም፡- በባህር ዳር፤ ፍኖተ ሰላም፤ እና ሞጣ - እነሴ ማዕከላት፤(የባህር ዳር አመልካቾች ምዝገባ በየአካዳሚክ ክፍሎች ሬጅስትራር ሲሆን የፍኖተሰላምና ሞጣእነሴ አመልካቾች ምዝገባ በርቀት ትምህርት ማዕከላት ይሆናል፡፡)
  • ለርቀት ትምህርት ፕሮግራም፡- በባህር ዳር፤ ጎንደር፤ ደሴ፤ ደብረ ብርሃን፤ አዲስ አበባ፤ ደብረ ማርቆስ፤ ፍኖተ ሰላም እና ሞጣ - እነሴ ማዕከላት፤(የሁሉም አመልካቾች ምዝገባ  በርቀት ትምህርት ማዕከላት ይሆናል፡፡)

ተጨማሪ ማሳሰቢያዎች፡-

  1. የቀድሞው ትምህርት ፖሊሲ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ተቀባይነት የለውም፤
  2. በዲፕሎማ የሚመዘገቡ አመልካቾች በምዝገባ ወቅት ኦፊሻል ትራንስክርፕት በፖስታ ሳጥን ቁጥር 79 ማስላክ አለባቸው፤
  3. በሀገር አቀፍ ደረጃ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ላልተዘጋጀላቸው የትምህርት ዘርፎች ተቋሙ የሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና መውሰድ አለባቸው፡፡ የፈተናው ቀን እና የቅበላ ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ቀን በውስጥ ማስታወቂያ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ ወይም የፌስቡክ ገጽ ወደ ፊት ይገለፃል፤
  4. በቂ የተማሪ ቁጥር የማያመለክትባቸው የትምህርት መስኮች አይከፈቱም
  5. ከዚህ በፊት ለመማር ተመዝግበው ባቋረጡት የትምህርት መስክ በተመሳሳይ የቅበላ ዓይነት መመዝገብ አይቻልም

ክፍያ የሚፈጸምባቸው የባንክ አካውንቶች

የመመዝገቢያ ክፍያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ገቢ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች፤

  1.  

ለቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ ማህበራው ሳይንስ፣ ሂውማኒቲስ፣ ትምህርትና ስነ ባህርይ ሳይንስ (PGDT)፣ግብርናና አካባቢ ሳይንስ እና ስፖርት አካዳሚ የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ፤

  1.  

ለኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት(EiTEX) የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ፤

ለባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት (BiT) የትምህርት መስክ አመልካቾች የመመዝገቢያ ክፍያ በቀጥታ ለኢንስትቲዩቱ ገንዘብ ተቀባዮች መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡

 

Contact

 

 Main Registrar Office 

Tel:   0582205934

 

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2019- Bahir Dar University