ቀን 03/02/2018 ዓ.ም

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው ወይም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉ፡- 

1ኛ. በመደበኛው መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾችን፤

2ኛ. በማታው መርሃ ግብር 2ኛ ዲግሪ አመልካቾችን፤

ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2018  ዓ/ም ድረስ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን አመልካቾች የሚያመለክቱባቸውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር እና የመግቢያ መስፈርቶችን ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በመደበኛው መርሃ ግብር ለሚማሩ የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዉ በሚኖሩት ክፍት ቦታዎች የዶርም አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች

  • የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፤ 

  • ኦፊሻል ትራንስክርፕት (ለሚመለከታቸው ብቻ)

  • በመስሪያ ቤት ስፖንሰርነት ለሚያመለክቱ አመልካቾች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት የስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  • ለማመልከቻ የተከፈለበት ደረሰኝ (Application fee 300 ብር)፣

 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የትምህርት ክፍሎች

1000224663378

 

ለግብርናና አካባቢ ሳይንስ፤ ለሂውማኒቲስ፤ ለቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ለሳይንስ፤ ለአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና፤ ለስነ-ምድር፤ ለሶሻል ሳይንስ፤ ለእንስሣት ህክምና፤ ለባዮቴክኖሎጂ፤ ለትምህርት፤ ለመሬት አስተዳደር፤ ለስፖርት እና ለህግ የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ፤

1000013094563

ለባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት (BiT) የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ

1000096185007

ለኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ (EiTEX) የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ

1000257812956

ለህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ

የማመልከቻ ቦታ፤

  • ምዝገባ የሚካሄደው በ”Online” በረ ገጽ http://studentportal.bdu.edu.et/ በመጠቀም ወይንም በሚመለከታቸው የአካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ

ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት