ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ የ2018 ዓ.ም የበጋ ስፖርት ስልጠና ምልመላ ሊያደርግ ነው፡፡
Peda Campus
16 Oct, 2025
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ የ2018 ዓ.ም የበጋ ስፖርት ስልጠና ምልመላ ሊያደርግ ነው፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ በ2018 ዓ.ም በተለያዩ የስፖርት አይነቶች እድሜያቸው ከ 8 አመት እስከ 16 ያሉ ታዳጊዎችን ለማሰልጠን ዝግጅቱን አጥናቋል፡፡
ስልጠናው የሚሰጠው ባለተሰጥዖ ተመዝጋቢዎች በሚመርጡት ስፖርት ማለትም፡
አትሌቲክስ
እግር ኳስ
እጅ ኳስ
መረቭ ኳስ
ቅርጫት ኳስ እንዲሁም በሌሎች ስፖርቶች እድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች ያሉ ታዳጊዎችን ለመመልመል ምዝገባ መጀመሩን እያሳወቀ ምዝገባው ባሉበት ሆነው በOnline ወይም ስፖርት አካዳሚ በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ ይሆናል።
📆 የምዝገባ ቀናት፡ ከጥቅምት 6-13 ቀንቀን 2018 ዓ.ም
📝የምዝገባ ሁኔታ፡
🕴️በአካል ስፖርት አካዳሚ ስፖርት ስልጠና ማስተባበሪያ ቢሮ ቁጥር 002 በመምጣት ወይም፤
⛓️💥ባሉበት በOnline ለመመዝገብ፡ ይህንን ይጫኑ
📌ማስታዎሻ፡
ነባር የአካዳሚው ስልጣኞችም በምልመላው ማለፍ የሚጠበቅባቸው ይሆናል።
 English
 English
       French
 French
 German
 German
