Henok

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ባለፉት ዓመታት ድንቅ ወጣቶችን እያፈራ ይገኛል

Sport Academy

10 May, 2025

 ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ የተገኘው የ 18 ዓመቱ ሔኖክ ይበልጣል በቢጫ ቲሴራ ባደገበት የመጀመሪያ አመት ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ላይ ይገኛል።

በሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ባህር ዳር ከነማ ሊጉን በ54 ነጥቦች ከሚመራው ኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጋር በነበረው ወሳኝ ጨዋታ ሙጅብ ቃሲምና ሔኖክ ይበልጣል ባስቆጠሯቸው ግቦች 2-1 በማሸነፍ ነጥቡን 46 በማድረስ ልዩነቱን ወደ 8 ዝቅ እንዲያደርግ ረድቶታል። በተለይም በ90+3 ደቂቃ በታዳጊው ሔኖክ የተቆጠረችው ግብ እጅግ ማራኪ ነበረች።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ባለፉት ዓመታት ድንቅ ወጣቶችን እያፈራ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም እድሜያቸው ከ7-18 ዓመት ያሉ ታዳጊዎችን አቅፎ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።