7ኛው አገር አቀፍ አመታዊ የምርምር ጉባኤ

7ኛው አገር አቀፍ አመታዊ የምርምር ጉባኤ እየተካሄደ ነው
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጥናት ተቋም 7ኛውን አገር አቀፍ አመታዊ የምርምር ጉባኤ በባሕር ዳር እያካሄደ ነው፡፡
በጉባኤው 14 የሚሆኑ የጥናትና ምርምር ጽሁፎች ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት እየተደረገባቸው ነው፡፡
በጉባኤው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ምንተስኖት አዘነ፤ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ተሰማ አይናለም፤ በአውሮፓ ህብረት ያልተማከለ የአደጋ ስጋት ቅነሳ አስተዳደርን ያልተማከለ ማድረግና ማጠናከር በኢትዮጵያ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ አያጣም ፈንታሁንና ከተለያዩ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎችና ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ ጥናት አቅራቢዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል፡
 
 
Share