ለሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጥናት ተቋም በ2013 የትምህርት ዘመን አዲስ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎችን በመደበኛ መርሃ ግብር ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
በማስተርስ ፕሮግራም

1. በአየር ንብረት ለውጥ እና ልማት (Climate Change and Development)
2. የኑሮ መተዳደሪያ እና ምግብ ዋስትና (Livelihoods and Food Security)
3. በአደጋ መከላከል እና ዘላቂ ልማት (Disaster Risk Management and Sustainable Development)
በፒኤች ዲ ፕሮግራም
1. PhD in Disaster Risk Science

ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ የማመልከቻ ቅጹን በማውረድና (Download) በመሙላት ትምህርቱ ወደሚሰጥባቸው የትምህርት ክፍሎች ሬጅስትራር E- mail, bduidrmfss.Registrar@bdu.edu.et አድራሻ በመላክ እንድታመለክቱ እያሳሰብን፡ሌሎች መሟላት የሚገባቸውን ዶክመንቶች፤ትምህርቱ የሚሰጥባቸውን የሙያ መስኮች እንዲሁም የትምህርት ክፍል ሬጅስትራሮችን E- mail አድራሻ ከድረ ገጻችን እንድትመለከቱ እያስታወቅን ወቅታዊውን የጤና ችግር በማስታወስ ለሁላችንም ጤና ሲባል በአካል የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን!!!

Share