የዐዉደ-ጥናት ተሳትፎ ጥሪ

የዐዉደ-ጥናት ተሳትፎ ጥሪ
================
ኢትዮጵያ የሃይማኖት ብዝኀነትና እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ አማኝ ሕዝብ ባለቤት መሆኗ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የሃይማኖቶች ጥናት በሃገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስካሁን በተደራጀ መንገድ እምብዛም አይታይም፡፡ በሌላ በኩል የሃይማኖት ቁርኝት ብዙም በተጠናከረ ሁኔታ በማይተገበርባቸዉ በርካታ የምዕራባዊያን ዩኒቨርሲቲዎች ከሃይማኖቶት ጥናት በተጨማሪ የሥነ-መለኮት ትምህርት መስጠት የተለመደ ነዉ፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሂዩማኒቲስ ፋከልቲ ይህንን የሃይማኖቶች ጥናት አስፈላጊነት በመገንዘብ አዲስ የድኅረ-ምረቃ ሥርዓተ-ትምህርት በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡ ከሥርዓተ-ትምህርቱ ዝግጅት ጎን ለጎን በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ የሚታየዉን ብዥታ ለማጥራትና የተሻለ ግብዛቤ ለመፍጠር “የሃይማኖቶች ጥናት አግባብነትና ሀገራዊ ፋይዳ” በሚል መሪ-ቃል የግማሽ ቀን ዐዉደ-ጥናት ግንቦት 26፣2014 ዓ.ም. በፔዳ ግቢ ትልቁ አዳራሽ (ኦዲቶሪየም) ያካሂዳል፡፡ በዐዉደ-ጥናቱ ላይ በዘርፉ የጠለቀ ዕዉቀትና ልምድ ያላቸዉ ምሁራን ገለፃ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ሀገራዊ ፋይዳቸዉ ከፍተኛ በሆኑ ጭብጦች ላይ ሰፊ ዉይይት ይደረጋል፡፡
እርስዎም በዚህ ዐዉደ-ጥናት ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ በአክብሮት እየጋበዝን ፕሮግራሙ የሚጀምረዉ ከጠዋቱ 2፡30 መሆኑን እንገልፃለን፡፡
Date: 
Wed, 06/01/2022
Image: 
Place: 
Bahir Dar University
Share