በውድድሩ የመጀመሪያውን ወርቅ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አገኘ
27 Jan, 2025
በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ በሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በወርልድ ቴኳንዶ በወንድ 68kg በአማኑኤል ዳንኤል አሸናፊነት የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 4ኛ ዓመት የህግ ተማሪው አማኑኤል ዳንኤል እልህ አስጨራሽ በሆነው ውድድር ከ 8፡00ስዓት እስከ ምሽቱ 2፡ዐዐስዓት ድረስ 6 ጨዋታዎችን በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።
ዩኒቨርሲቲያችን በአራት የውድድር አይነቶች በመሳተፍ ላይ ሲሆን ከአራቱ አንዱን አስቀድሞ ወርቁን በእጁ ማስገባት ችሏል።