የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በጅማ ከተማ ይካሄዳል።

ፔዳ ግቢ

08 Nov, 2025

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በጅማ ከተማ ይካሄዳል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 49 ዩኒቨርሲቲዎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በጅማ ከተማ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማህበር አስታውቋል።

 ቀደም ብሎ በአምስት ክላስተሮች ውድድር ለማካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም አዘጋጅ ተቋማት ዝግጁ ባለመሆናቸው ሀገር አቀፍ ፌስቲቫል ለማከናወን መወሰናቸውን የማህበሩ ፕሬዚዳንት አባይ በላይሁን መናገራቸውን የባህልና ስፖርት ሚንስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

ከባለፈው ዓመት በበለጠ በሁለቱም ጾታ በርካታ ተወዳዳሪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ፌስቲቫል ከዚህ ቀደም ሀገርን በተለያዩ መድረኮች መወከል የቻሉ ስፖርተኞች የፈሩበት መሆኑን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ የዘንድሮውም የታቀደለትን ግብ እንዲመታ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ አስረድተዋል።

ፌስቲቫሉ በ15 የስፖርት አይነቶች ከጥር 9-24 ድረስ የሚካሄድ ሲሆን ለውድድሩ በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል፡፡

ለ8 ዓመት በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ባፈው ዓመት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በአምስት የስፖርት አይነቶች መካሄዱም ይታወሳል፡፡