Summar
በክረምት መርሀ-ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት መግቢያ መስፈርት
12 ክፍል ዉጤት የሚመዘገቡ ተማሪዎች ፈተና በወሰዱበት አመት የት/ት ሚኒስቴርን የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ መስፈርት ያሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ድግሪ አስይዘዉ ለሚመዘገቡ አመልካቾች በማንኛዉም የትምህርት መስክ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ዲፕሎማ አስይዘዉ ለሚመዘገቡ አመልካቾች በዲግሪ መርሃ-ግብር መመዝገብ የሚችሉት ዲፕሎማቸዉ ቀጥተኛ ተዛምዶ ሲኖረዉ ነዉ፡፡
በ 12ኛ ክፍል ዉጤት ከሚመዘገቡ ተማሪዎች በስተቀር ሁሉም አመልካቾች ቢያንስ የ1 ዓመት የስራ ልምድ ማስረጃ ህጋዊ እዉቅና ካለዉ መስሪያ ቤት(ድርጅት) ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
ዲፕሎማ አስይዘዉ ለሚመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን የዲግሪ እና 12ኛ ክፍል የትምህርት ዝግጅት ያላቸዉ የመግቢያ ፈተና እንዲወስዱ አይጠበቅባቸዉም፡፡
ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ አስይዘዉ ለሚመዘገቡ አመልካቾች፣ በማመልከቻ ወቅት Official Transcript መድረስ ይኖርበታል፡፡
የማመልከቻ ክፍያ (Admission Fee) አይመለስም፡፡
በአስረጅነት የሚቀርቡ ማንኛዉም መረጃዎች ኦርጅናሉንና ከሁለት ፎቶ ኮፒ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የመሰናዶ ፈተና ለወሰዱ የት/ት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት፡-
• በ2010 ዓ.ም 295 እና ከዚያ በላይ
• በ2009 ዓ.ም 295 እና ከዚያ በላይ
• በ2008 ዓ.ም 295 እና ከዚያ በላይ
• በ2007 ዓ.ም 275 እና ከዚያ በላይ
• በ2006 ዓ.ም 250 እና ከዚያ በላይ
• በ2005 ዓ.ም 265 እና ከዚያ በላይ
• በ2004 ዓ.ም 265 እና ከዚያ በላይ
• በ2003 ዓ.ም 265 እና ከዚያ በላይ
• በ2002 ዓ.ም 280 እና ከዚያ በላይ
• በ2001 ዓ.ም 200 እና ከዚያ በላይ
• ከ1995-2000 ዓ.ም የመሰናዶ ፈተና ወስደው ውጤት ያስመዘገቡ
• ከ1994 ዓ.ም በፊት ዲፕሎማ ያጠናቀቁ
• ከ1994 ዓ.ም በፊት ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በዲፕሎማ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ እና ከ1994 ዓ.ም በኋላ ከየትኛውም ተቋም ትምህርታቸውን በ10+3 ወይም በደረጃ -4 ያጠናቀቁ ደረጃ-4 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚያቀርቡ