
ቀን፡13/ 05/ 2013 ዓ.ም
የጥሪ ማስታወቂያ
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም መደበኛ (የቅድመ ምረቃና ፒ.ጂ.ዲ.ቲ)2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ለነበራችሁ ተማሪዎች በሙሉ
በ2012 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና (COVID-19) ወረርሽኝና በሐሃገራችን በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የቅድመ ምረቃና ፒ.ጂ.ዲ.ቲ መማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በመጀመሪያው ዙር ተመራቂ ተማሪዎችን መቀበላችን ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት የዩኒቨርሲቲያችን የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ያልሆናችሁ 2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ ከየካቲት 04 እስከ 05 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት በአካል ቀርባችሁ በየኮሌጆቻችሁ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ከዚህ ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የሬጅስትራርና አሉምናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
Main Registrar Office
Tel: 0582205934
Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2019- Bahir Dar University