
ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም
የተሻሻለ የጥሪ ማስታወቂያ
ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ባደረገው ግምገማ በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር እንደገና መቀጠል እንደሚችል ማረጋገጡን ተከትሎ ተማሪዎች በተለያዩ ዙሮች ወደትምህርት ገበታቸው እየተመለሱ መማር ማስተማሩ እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ብቻ የምዝገባ (Registration) ጊዜ ጥቅምት 14-15 ቀን 2013 ዓ.ም ሆኖ ትምህርት የሚጀምርበት ቀን (Day-One-Class-One) ደግሞ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ትናንት ማሳዎቃችን ይታወሳል፡፡
ይሁንና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች መግቢያ ጊዜ ከጥቅምት 23-30 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሆን ትናንት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የዩኒቨርሲቲያችን የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች (የመጀመሪያ ዲግሪና የፒ.ጂ.ዲ.ቲ መደበኛ ብቻ) የመግቢያ ጊዜ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ከይቅርታ ጋር እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በሚመለሱባቸው ጊዜያት ከትራንስፖርት ጋር በተያያዘ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሰረት የሚቀየር ነገር ቢኖር አሁንም በማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አሉምናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
Main Registrar Office
Tel: 0582205934
Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2019- Bahir Dar University