
በ2013 ዓ/ም የነፃ ትምህርት ተጠቃሚ ለመሆን ለሚፈልጉ አመልካቾች
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ/ም በመደበኛ መርሃ ግብር በሚሰጡ የ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በሚኖሩት ክፍት ቦታዎች የነፃ ትምህርት እድል ለመስጠት አቅዷል፡፡ እድሉን ላገኙ እጩዎች ዩኒቨርስቲው የትምህርት ወጭዉን ብቻ (የምርምር፣ የምግብ፣ የዶርምና የህክምና አገልግሎት ወጭን ሳይጨምር) የሚሸፍን መሆኑን ይገልፃል፡፡ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
ሀ) በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት (እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2013) የማመልከቻ ፎርማሊቲዎችን አሟልቶ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፤
ለ) በምዝገባ ወቅት ኢፊሺያል ትራንስክሪፕት (Official Transcript) ለሬጅስትራር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
ሐ) የመጀመሪያ ድግሪ አማካይ ውጤት ለወንዶች 3.50፣ለሴቶች፣ለአካል ጉዳተኞችና የታዳጊ ክልል አመልካቾች 3.00 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፤
መ) የመግቢያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ማምጣት የሚችሉ፤
ሠ) ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስራ አጥ ማስረጃ፤
ረ) የነፃ ትምህርት ዕድል ለማግኘት ማመልከትና ለነፃ ትምህርት የተዘጋጀውን ፎርም መሙላት ይጠበቅባቸዋል፤
Main Registrar Office
Tel: 0582205934
Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2019- Bahir Dar University