Latest News

ለሁለት ወራት ሲካሄድ የነበረው ስፖርታዊ ውድድር ፍፃሜውን አገኘ 

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን ከሚያዚያ 1 እስከ ግንቦት 30፣ 2013 ዓ.ም ድረስ የተካሄደው የማህበረሰብ የውስጥ ስፖርት ውድድር ፍፃሜውን አገኘ፡፡

ውድድሩ ታራሚዎችን በስነ ምግባር እና በዕውቀት በማነፅ ውጤታማ፣ ተወዳዳሪ እና አምራች ዜጋን ለማፍራት አላማ አድርጐ ለ2 ወራት በ4 የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ እንደነበር አዘጋጆች ጠቁመዋል፡፡

በፍፃሜው ውድድር በገመድ ጉተታ ዞን 1፣ በቫሊቮል ዞን 4፣ በእግር ኳስ ዞን 5 የተባሉ ማረሚያ ቤት ቡድኖች በጨዋታው አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

የፍፃሜ መርሃ-ግብሩን በንግግር የከፈቱት በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤቶች የማረም፣ ማነፅ የስራ ሂደት ቡድን መሪ አቶ ግርማ ጥሩነህ ስፖርት አካዳሚው ሀሳብ ከማመንጨት ጀምሮ የማህበረሰቡ አካል የሆኑትን ታራሚዎችን በስፖርታዊ ውድድር ማሳተፋቸው በስነ-ልቦና የጠነከረ ንቁ ዜጋን ከማፍራት አኳያ ፋይዳው የጐላ ነው ብለዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ዲን ዶ/ር ዳኛቸው ንግሩ ለአሸናፊዎች የዋንጫ ሽልማት በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት ስፖርት ለወዳጅነት፣ ለአንድነት እና ለፍቅር የሚያደርገውን እስተዋጽኦ ተገንዝበው ታራሚዎች ባሉበት ቦታ ስፖርታዊ ውድደሩ ያስፈልጋቸዋል በሚል ሀሳብ ላመነጩት ለመምህር ዳንኤል ጌትነት እና ለረዳት መምህር ጠቢቡ ሰለሞን እንዲሁም በግቢው በነበረው ቆይታ ለታራሚዎች እና ቅንነት፣ ፍቅርና አገልጋይነትን በተግባር ላሳዩት ለማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር ውብሽት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ውድድሩ በአራት የስፖርት አይነቶች በወንዶች ብቻ ለሁለት ወር መካሄዱን አውስተው በቀጣይ አመት በሴቶቸም ውድድሩን በማስቀጠል ለታራሚዎች የአንደኛ ደረጃ ስልጠና በመስጠት ስፖርቱ ቀጣይነት እንዲኖረው እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን በመወከል የተገኙት የፕሬዝዳንት  ጽ/ቤት  ኃላፊ  አቶ  አራጋው  ብዙዓለም  በበኩላቸው በዚህ መልኩ አሰፈላጊ ነው በሚል ስታደርጉት የነበረው የስፖርት እንቅስቃሴ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም እንደ ማህበረሰብ አገልግሎት ስፖርቱን ለመደገፍ ፍቃደኝነታችን እየገለፅን በእስካሁኑም ለደገፋችሁ ድርጅቶች ምስጋናየን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በሁለቱ ወራት ስፖርታዊ ውድድር የተሻለ አፈፃፀም ላደረጉ የቤንማስ እና አዲስ አምባ ሆቴልን ጨምሮ ለባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤቶች መምሪያ እንዲሁም ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ አመራሮችና ባለሙያዎች የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ 

 

CANAG project produces Synthesis reports and manuals

CANAG project, a project implemented by a collaborative effort of BDU, AAU, MekU, JU, HawU and WUR produced 31 synthesis reports and manuals. Herewith are the links for the documents produced and enjoy reading.

 1. CANAG BDUC special study on the enabling environment for NSA.pdf

https://drive.google.com/file/d/1BJdY54j-ADN3OvVFsSG2RAhL5v-SeIib/view?usp=sharing_eil_dm&ts=60b9e440

 1. CANAG JUC booklet on PICS bags for enset processing technology.pdf
 2.  
 3. CANAG JUC booklet on pot-in-pot cooler technology.pdf

https://drive.google.com/file/d/10nl6Wl_lPETmixj_ZgW1AqWuD2iXvPAK/view?usp=sharing_eil_dm&ts=60bf075a

 1. CANAG JUC manual on home garden technology.pdf
 2.  
 3. CANAG JUC manual on sack garden technology.pdf
 4.  
 5. CANAG JUC special study on improved enset processing technology.pdf
 6.  
 7. CANAG JUC special study on improved enset processing technology.pdf

https://drive.google.com/file/d/1NTe3yF9WA3y-FhDFwtDx8xWxpGrLX7HR/view?usp=sharing_eil_dm&ts=60bf073c

 1. CANAG JUC special study on vegetable seed system.pdf
 2.  
 3. CANAG MUC booklet on pot-in-pot cooler technology.pdf
 4.  
 5. CANAG MUC booklet on water lifting and transport technology.pdf
 6.  
 7. CANAG MUC manual on dairy goat technology.pdf
 8.  
 9. CANAG MUC manual on home garden technology.pdf
 10.  
 11. CANAG MUC manual on home garden technology.pdf
 12.  
 13. CANAG National synthesis report on technology validation.pdf
 14.  

 

 1. CANAG National synthesis report on intra-household dynamics pilots.pdf
 2.  
 3. CANAG National synthesis report on Dietary Diversity Score baseline vs. endline.pdf
 4.  
 5. CANAG MUC special study on intra household dynamics pilot.pdf
 6.  
 7. CANAG MUC manual on home garden technology.pdf
 8.  
 9. CANAG HUC booklet on enset scraper technology.pdf
 10.  
 11. CANAG HUC booklet on fuel saving stove technology.pdf

https://drive.google.com/file/d/1aYt3NItdz8cpyI4n7TjZkQH25NxYOxo1/view?usp=sharing_eil_dm&ts=60bf06d5

 1. CANAG HUC special study on beetroot and carrot fertilizer responses to FYM vs NPS .pdf
 2.  
 3. CANAG HUC special study on intra household dynamics pilot.pdf
 4.  
 5. CANAG JUC booklet on avocado harvester technology.pdf
 6.  
 7. CANAG JUC booklet on avocado harvester technology.pdf

https://drive.google.com/file/d/1Fii8hr0DNZjbeWSW0Ojfb3g70K1Y2RIw/view?usp=sharing_eil_dm&ts=60bf06b7

 1. CANAG HUC booklet on enset scraper technology.pdf
 2.  
 3. CANAG BDUC manual on improved chicken production technology.pdf
 4.  
 5. CANAG BDUC manual on improved chicken production technology.pdf

https://drive.google.com/file/d/1qzhB_IBfdoF4WHtxhprQ9FA1nT_Y8S3d/view?usp=sharing_eil_dm&ts=60bf0698

 1. CANAG BDUC manual on home garden technology.pdf
 2.  
 3. CANAG BDUC booklet on potato harvester technology.pdf
 4.  

 

 1. CANAG Activity completion report.pdf

Top of Form

https://drive.google.com/file/d/1g7DJpH_AgGNAS901K3iAr1eiHWZrz17k/view?usp=sharing_eil_dm&ts=60bf0681

 1. CANAG Activity completion report.pdf
 2.  
 3. CANAG AAUC manual on home garden technology.pdf
 4.  
 5. CANAG BDUC special study on the enabling environment for NSA.pdf

https://drive.google.com/file/d/1BJdY54j-ADN3OvVFsSG2RAhL5v-SeIib/view?usp=sharing_eil_dm&ts=60b9e409

 1. CANAG AAUC booklet on pot-in-pot cooler technology.pdf

https://drive.google.com/file/d/1Ho1jPrx8gV-RiTQwYKv0W0SD1gLaNZ6H/view?usp=sharing_eil_dm&ts=60b9e402

 

 

የትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ኮሌጅ 38ኛውን ዓመታዊ አለማቀፍ የግንቦት አውደ-ጥናት አካሄደ
***************************************************************
በሙሉጌታ ዘለቀ
የትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ኮሌጅ 38ኛውን ዓመታዊ አለማቀፍ የግንቦት አውደ-ጥናት Ethiopia’s Progress towards achieving sustainable development በሚል ርዕስ በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንቦት 27 እና 28/2013 ዓ.ም አካሂዷል ፡፡
 
በአውደ-ጥናቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ለታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ እና ለኮንፍረንሱ አዘጋጆች የምስጋና መልእክታቸውን አስተላልፈው እንደሀገር የምንከተለው የትምህርት ስርዓት የመጭውን ትውልድ እጣ-ፋንታ የመወሰን ሀይል ስላለው በዋናነት ብቁ መምህራንን ከማፍራት አንፃር በመምህራን ስልጠና እና ትምህርት ስርዓቱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም የሴሚናሩ ተሳታፊዎች በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህረት ተቋማት የመጡ በመሆኑ ዶ/ር ፍሬው ስለባሕር ዳር ከተማና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አጠር ያለ ገለፃ አድርገዋል፡፡
 
 
በአውደ-ጥናቱ በኢትዮጵያ የUNESCO የትምህርት ዳይሬክተር የሆኑት Yumiko Yokozeki (PhD) በበይነ መረብ “The Role of Teachers in Achieving SDGs” በሚል ርዕስ ፁሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም የሳይንሰና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አማካሪና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ያለው እንዳወቀ “ Addressing quality education issues in higher education” ፣ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር አለማየሁ ቢሻው “Inclusive and equitable quality Secondary education” እንዲሁም የቀድሞ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩና በአሁኑ ሰዓት በእንግሊዝ ሀገር University of Cambridge የትምህርት ፋኩልቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር ዳዊት ጥበቡ “Understanding the impacts of large-scale educational reforms on primary school students learning progress: Who is benefiting from the reforms”? በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፁሁፎችን አቅርበው በተጨማሪም የአውደጥናቱን ጭብጥ አስመልክቶ ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
በዚህ ዓመታዊ አለማቀፍ አውደ-ጥናት ከ16 በላይ የሚሆኑ ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ታደሰ መለሰ በአውደጥናቱ መዝጊያ እንዳሉት የቀረቡት የጥናት ወረቀቶች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
 
በአውደ-ጥናቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ጥናትና ምርምር አቅራቢዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ባለሙያዎች፣ መምህራንና ተማሪዎች ታድመውበታል፡፡
 
በመጨረሻም በአውደ-ጥናቱ ላይ የጥናት ወረቀት ላቀረቡ መምህራን የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

 

ለተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

በሙሉጎጃም አንዱዓለም

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ከማህበራዊና ጤና አገልግሎት ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ለመደበኛ ተማሪዎች  በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለ2 ተከታታይ ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

የስልጠናውን የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ብርሃኔ መንግስቴ የስልጠናው ዋና ዓላማ ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያውቁ፣በራስ መተማመናቸውን እንዲያዳብሩ  እንዲሁም ከስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ለሌሎች በማጋራት ባሉበት ግቢ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ ታልሞ መሆኑን ገልፀዋል፡፡  

ዳይሬክተሯ አክለውም ከአሁን በፊት የነበረው አሰራር የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እንደገቡ ስልጠናው ይሰጥ እንደነበር ጠቁመው በያዝነው ዓመት ግን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አንደኛ ዓመት ተማሪዎች በመዘግየታቸው በመማር ላይ ላሉት በተለይም በክበባት የታቀፉ ሆነው  ከሁሉም ግቢና ባች ለተውጣጡ ተማሪዎች ስልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

ማህበራዊና ጤና አገልግሎት ልማት ድርጅት ከዩኒቨርሲቲው ጋር አብሮ ለመስራት በያዘው ውል መሰረት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነና የተለያዩ ስልጠናዎችንም ለተለያዩ አካላት በመስጠት ላይ እንደሆነ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ 

አሰልጣኞችም ከአሁን በፊት የህይዎት ክህሎት ስልጠና የወሰዱ የዩኒቨርሲቲው መምህራን መሆናቸው ተገልጿል፡፡ 

Bahir Dar Energy Center of Bahir Dar Institute of Technology-Bahir Dar University organizes a site visit to the living lab research and community engagement project at Dangisheta Wareketo Kebele in Dangla District for the management team.
=============================================
The Management team, led by Dr. Seifu Admasu, Scientific Director for Bahir Dar Institute of Technology, visited the progress of the living lab project at Dangisheta site in Dangila woreda on May 29, 2021.
The living lab, a research and community engagement project is run by a collaborative effort of Bahir Dar Institute of Technology and Technical University of Munich (TUM) based on the agreement signed as part of the project on Sustainable Energy and Entrepreneurship in Global South from March 2020. Bahir Dar Institute of Technology has prepared the design and sizing of the living lab that can irrigate over 10 hectares of land and electrify about 100 households. About half of the budget required is allocated by TUM through German Academic Exchange Service (DAAD) and the rest is to be covered by Bahir Dar University. According to the site visit, a borehole of about 160m depth was successfully completed. Based on the pump test, its yield found to be more than 30 liters per second.
After a visit to the progress of the project, a brief discussion was held between the community and the management team. The former Scientific Director of BiT, Dr. Nigus Gabbiye, introduced the overview of the project to the community and BiT management team. Dr Mekuanint Agegnehu, Deputy Scientific Director for Research and Community Services of the institute, on his part, briefed the community about the community based activities being done by BiT-BDU.
Dangisheta Wareketo Kebele Administrator, Mr. Yenew Abera, and Water Resources Team leader of Dangla District, Mr. Abebe Bitew, extended their gratitude to BiT-BDU and vowed on behalf of the community to ensure the sustainability of the implemented project and to commit to the remaining phases of the living lab until completion.
Dr. Seifu Admasu, Scientific Director of BiT-BDU, has made a closing remark and gave directions to the community and his team on the way forward. In his clothing remark, Dr. Seifu, appreciated the hospitality of the community and leaders of the municipality, and appreciated their close working with the institute since 2014. Finally, he wrapped up his remarks by advising the community to own the project and be a model community. Moreover, the Scientific Director commented that the project team shall focus on defining the irrigation land, identifying the infrastructures needed and discussing continually with the community on the management of the remaining phases of the project for a successful completion of the project.

ለተከታታይ ስድስት ሳምንታት ሲካሄድ የነበረው ውድድር ተጠናቀቀ

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ እና በባሕር ዳር ማረሚያ ቤቶች ትብብር ለተከታታይ ስድስት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየውና ታራሚዎችን በስነ ልቦናና በማህበራዊ መስተጋብር እንዲጎለብቱ ለማገዝ ታቅዶ የተከናወነው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቋል፡፡  

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ ክፍል መምህርና የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ዳንኔል ጌትነት እንደተናገሩት ከእለቱ ውድድር በፊት ለተከታታይ ስድስት ሳምንታት በላይ ለሚሆን ጊዜ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  ስፖርታዊ ውድድሮች መካሄዳቸውን አውስተዋል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ስፖርታዊ ጨዋነትን ተላብሰው በመጫዎት ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ ብቁና ምርታማ እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

መምህር ዳንኤል አያይዘውም ካለው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ድርሻ አንፃር ለዚህ አይነት ፕሮጀክት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል በማለት ዩኒቨርሲቲው ከሚመለከታቸው አካላት ጋራ በመተባበር መሰል የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በስፋት ማከናወን ቢቻል መልካም ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ውድድሩ  መረብ ኳስ፣ እግር ኳስ፣ ገመድ ጉተታ እንዲሁም የአትሌቲክስ ውድድርን ያካተተ ሲሆን በእግር ኳስ ባሕር ዳር ማረሚያ ቤት ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ፤ በቫሊቮል ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ 2 ለ 1 በማሸነፍ ሁለቱም የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በዕለቱ በእንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ ቴንስ ፌደሬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ይልማ ከፋለኝ ስፖርት አካዳሚው የሚሰጠውን የማህበረሰብ አገልግሎት አድንቀው ከዚህ ባሻገር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዕድሚያቸው ከ12 ዓመት በታች የሆኑ 40 ህፃናትን በግራውን ቴንስ እያሰለጠነ እንደሚገኝም አውስተዋል፡፡ ይህንም ለመደገፍ ፅ/ቤታቸው ለቴንስ ፐሮጀክት ሰልጣኞች አገልግሎት የሚውል ከዛሬው ጋር ለሁለተኛ ጊዜ የቁሳቁስ ድጋፍ ማደረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ 

ለተወዳዳሪዎችም የአዲስ አምባ እና ቤንማስ ሆቴሎች የማልያ ድጋፍ ማድረጋቸውን ከአዘጋጆች ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Graduate students from Africa participate in sport competition

Graduate students who came to BDU for the 1st African Graduate Students Conference Bahir Dar University participate in a friendly sport competition with graduate students from Bahir Dar University. The competition was on two sport activities: football and rope pulling. Bahir Dar University graduate students football team beat a team made out of graduate students from all other universities in Ethiopia (3-o).

In another competition, the visiting team beat rope pulling team of Bahir Dar University 2-0.

 It is believed that sport activities with the likes of these ones will have a great role to play in increasing bond among graduate students in Africa that can be translated into cooperation in research and other academic engagements.

1st African Graduate Students Conference convened by Bahir Dar University starts today

The 1st African Graduate Students Conference which was organized by Bahir Dar University with the theme “an integrated, prosperous and peaceful Africa driven by its graduate students towards agenda 2063” commenced today.

Opening session of the conference was moderated by Dr Dawit Amogne a teacher and researcher at BDU. He welcomed all and invited Dr Mulugeta Admasu, chairperson of the conference organizing committee and Executive Dean of Graduate Studies, BDU. Dr Mulugeta Admasu welcomed all to the conference and briefly stated the objective of the conference. He said the conference is a good platform for graduate students to share their recent research works to their fellow graduate program students, researchers and experienced professionals across the academia. He added the event will help facilitate young researchers to create networks for a profound scientific problem solving researches.

Dr Firew Tegegne president of bahir Dar University on his part welcomed all to the beautiful Bahir Dar City and to Bahir Dar University. He mentioned that Bahir Dar was recognized as UNESCO’s learning city and Lake Tana area was recognized as Biosphere Reserve. The president made a brief but comprehensive account of the achievements of Bahir Dar University in the journey to becoming a research intensive University in areas of research production and dissemination, education, internationalization, etc.

Speaking about the day’s event, the president highlighted that the event is an integral part of the university’s ongoing effort to initiate, support, promote and disseminate research and knowledge from multidisciplinary areas. He highlighted that BDU works to deconstruct the wrong attitude towards indigenous knowledge through research based dialogues using conferences like the current one. According to the president, in its endeavor to internationalization, Bahir Dar University has been producing marine professionals for the international labor market and the professionals are ambassadors of BDU while cruising to different parts of the world. He also mentioned the graduate students from Africa, Europe and the USA BDU hosts as an indicator of BDU’s internationalization activities. The president remembered the debate held the previous day among political party representatives in the same hall /Wisdom Hall/ the current conference is taking place in front of scholars from all public Universities. He emphasized the role that higher institutions play in the overall development of a country from producing successful human resource personnel to unfolding policy impact innovative research ideas. Dr Firew Tegegne finally thanked sponsors and all people who participated in organizing the conference which is the first in its kind and world class by any standard.

His Excellency Professor Afework Kassu state Minister for MoSHE took the stage to officially open the conference. The professor welcomed all and congratulated Bahir Dar University for successfully organizing such a brand academic conference which has to develop and be emulated by other universities in the country and beyond.

In his opening address, professor Afework focused on three points oriented from policy perspective:  policy context to research, the notion of connecting students’ research endeavors to national holistic development and issues to be focused for a better future. Professor Afework advised the participants to orient their researches in light of the policies and the 17 Sustainable Development Goals /SDGs/ crafted by Africans for Africa. He said researchers and scholars shall consider the indicators of the SDGs and bring those indicators down to their context and make something relevant to the wider academic discourse.

Professor Afework reiterated the importance of connections, both domestic and international, graduate students should create to benefit both professionally to produce quality and reputable research outputs and financially to win research grants. The state Minister also mentioned names of Ethiopian prominent academic figures to get connected to and benefit from their vast experience and knowledge. He also encouraged participants to join professional associations which create an environment for academicians and researchers to benefit in various ways. The professor finally wishes participants to have fruitful discussion in the days ahead.

The morning session was packed with very inspiring and critical keynote Speeches by three Prominent Ethiopian Professors lending the participants to the afternoon session which is learnt to take place in five parallel sessions entertaining different themes.

In this conference, graduate students from almost all universities in Ethiopia, professors, Dr Eshete Dejen and Dr Kebede Kassa from IGAD, government concerned bodies from different sector bureaus and others participated.

In the conference, three keynote speeches, a total of 120 presentations (70 oral and 50 poster presentations) are expected to be delivered.

"የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት" በሚል ርዕሰ  በተፎካካሪ ፓርቲዎች የክርክር መርሃ-ግብር ተካሄደ

=============================================================

በሙሉጌታ ዘለቀ

የኢፌድሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ስድስተኛውን ሐገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ  ግንቦት 19/2013 ዓ.ም የትምህርት ጥራትና አግባብነት" በሚል ርዕስ ባዘጋጁት የክርክር መድረክ ላይ ሰባት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተገኝተው በፕሮፌስር ዳንኤል ቅጣዉ እና በፕሮፌሰር ያለው እንዳወቅ  አወያይነት በጥበብ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ክርክራቸውን አድርገዋል፡፡

የአብክመ ም/ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት የኢትዮጵያ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ላይ የኢትዮጵያ ምሁራን  አሻራቸውን ማስቀመጥ ባለመቻላቸው  እና የንግግር ባህልን  ባህሪያችን ባለማድረጋችን ሀገራችን አሁን ያለችበትን ሁኔታ መመልከት የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርትን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መነጋገር ባህል ማድረግ አለመቻላችን የጠቆሙት ም/ርዕሰ መስተዳድሩ  ይህ የክርክር መድረክ አይን ከፋች እንቅስቃሴ በመሆኑ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

የፕሮግራሙ አላማ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን  በአገራዊ ጉዳዮች ላይ በሳል ዉይይቶችን በማድረግ በሀገር ግንባታ እና እድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጡ በሚችሉ የስርዓተ ትምህርት ማሻሻልና በመምህራን ስልጠና እንዲሁም የትምህርት ግብዓቶች ላይ ከፍተኛ ስራ በመስራት የድርሻዉን እንዲወጣ ለማድረግ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በኢፈድሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተደጋጋሚ የውይይት መድረኮችን ለማዘጋጀት ከፍተኛ ተነሳሽነት ያለ መሆኑን የሳይንሰና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ገልፀዋል። በክርክሩ እንዲሳተፉ ጥሪ ከተደረገላቸው 15 የፖለቲካ ፓርቲዎች  መካከል ሰባት (7 ) ፓርቲዎች በክርክሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡ በክርክሩ ከተሳታፊ ለተነሱ ጥያቄዎች  ተሳታፊ  የነበሩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡  

በፕሮግራሙ    የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፍሬዉ ተገኘ ጨምሮ የአብክመ ም/ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ፣ የሳይንሰና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፣ ፕሮፌስር ዳንኤል ቅጣዉ እና ፕሮፌሰር ያለው እንዳወቅ እና በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በመወከል በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በመጨረሻም በውይይት መድረኩ ላይ ለመታደም የመጡ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በመወከል የተገኙ  እንግዶች ከሰዓት በኋላ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲንና የባሕር ዳር ከተማን ጎብኝተዋል፡፡

 

እንኳን ደስ አላችሁ!
=========
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግንቦት 21፣ 2013 ዓ.ም. ሐኪሞችን
በሕክምና ዶክትሬት ያስመርቃል!!
 
እንኳን ደስ አላችሁ ተመራቂ ሐኪሞቻችን!

Pages