Latest News

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተቋም የስርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሄደ
---------------------------------------------------------------------------------------------
በሙሉጌታ ዘለቀ
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጥናት ተቋም የአደጋ መከላከልና ዘላቂ ልማት ትምህርት ክፍል አዲስ ለሚከፍተው የ3ኛ ድግሪ የአደጋ ስጋት መከላከል ሳይንስ ጥናት ዘርፍ የስርዓተ ትምህርት ግምገማ በግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ተካሂዷል፡፡
 
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር አዳነ ተስፋዬ በአሁኑ ጊዜ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውንና በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ተናግረው ይህንን አደጋ የሚቀንሱና የሚተነትኑ እንዲሁም አመራር የሚሰጡ ባለሙያዎችን ለማፍራት የዚህ ፕሮግራም መከፈት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ወደ እለቱ ዋና ውይይት እንደ መንደርደሪያ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተቋም ተመራማሪና መምህር የሆኑት ዶ/ር ምንተስኖት አዘነ አዲስ ስለሚከፍተው የፍልስፍና ዶክትሬት ዲግሪ የስርዓተ ትምህርት ረቂቅ እና ስለተደረገው የዳሰሳ ጥናት አቅርበዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር በላይ ስማነ እና ፕሮፌሰር ወልደ አምላክ በእውቀት በረቂቅ ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ጥልቅ የሆነ ግምገማ ቀርቧል፡፡ እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት በመጡ እንግዶችና ታዳሚዎች ሀሳቦችና አስተያየቶች ቀርበው በስርዓተ ትምህርት አርቃቂ ኮሚቴውና በፕሮግራሙ ተሳታፊ በሆኑ መምህራን ግብረ-መልስ እና ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
 
በመጨረሻም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር አዳነ ተስፋዬ በውይይቱ ላይ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር የፕሮግራሙ መከፈት ለሀገራችን ብሎም በአፍሪካ ደረጃ ተቋሙ ተወዳዳሪ እንዲሆንና የሰለጠኑና ተወዳዳሪ የሆኑ ባለሙያዎች ለማፍራት ተቋሙን በሰው ሀይል፣በቤተ ሙከራና በትምህርት ቁሳቁስ የተሟላ በማድረግ ረገድ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በኩል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር አዳነ አክለውም ከሚቀጥለው መስከረም 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሁለት ወይም አራት የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችን ተቋሙ ማስልጠን እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡ በእለቱ የተገመገመውን የስርዓተ ትምህርት ረቂቅ አስመልክቶ ዳይሬክተሩ ሲናገሩ ተቋሙ የተሰጡትን ግብዓቶች በማካተት እንደገና በባለሙያ እንደሚያስተች እና አስፈላጊውን በማሟላት ወደ ተግበራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
 
 
 
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኤች አይ ቪ ጋር በሚኖሩ የአስተዳደር ሰራተኞችና መምህራን በተቋቋመው የእድገት ስራ ማህበር አማካኝነት 25 ለሚሆኑ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለልደት በአል መዋያ የሚሆን ብር 400.00 ለእያንዳንዳቸው ተለግሷል፡፡
እርዳታው የተደረገላቸው የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በድል ችቦ፣ እውቀት ፋና፣ ሹም አቦ፣ መስከረም 16 እና ፈለገ አባይ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ወላጅ አልባ ልጆች እንደሆኑም የታወቀ ሲሆን ከዚህ እርዳታ ባሻገር በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመደበኛው ፕሮግራም ትምህርተቸውን ለሚከታተሉ ሁለት ከቫይረሶ ጋር ለሚኖሩ ተማሪዎች ቋሚ የቁሳቁስ እርዳታ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡
ማህበሩን 31 ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ የተቋሙ ሰራተኞች የመሰረቱት ሲሆን ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ፎቶ በማንሳት እና የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ ከፍቶ በመስራት ገቢ እንደሚያገኝ በዩኒቨርሲቲው የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት ገልፀዋል፡፡

Geospatial Data & Technology Center is giving training

Geospatial Data & Technology Center (GDTC) is providing a training entitled "Climate Data Analysis and Graphic Visualization using MATLAB" for Bahir Dar University staff and postgraduate students (Masters and PhD). The training lasts for five days, beginning December 31, 2019. We will give more information on the training in the days ahead.

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ማበልፀጊያ ማዕከል (STEM CENTER) ተግባር ተኮር የሳይንስ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በሸጋው መስፍን

ሥልጠናው እስራኤል ሀገር ከሚገኘው ዋይዝማን ኢንስትቲዩት ኦፍ ሳይንስ (WEIZMANN INSTITUTE OF SCIENCE) በመጡ ምሁራን ከታህሳስ 13/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በዩኒቨርሲቲው የሳይንስ ማበልፀጊያ ማዕከል (STEM CENTER) መሰብሰቢያ አዳራሽ የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው ዋና ትኩረት በአካባቢያችን በሚገኙ ቁሳቁሶች እንዴት ተግባር ተኮር በሆነ መንገድ ሳይንስን ማስተማር እንደሚቻል ለሰልጣኞች ማሳየት ነው፡፡ ስልጠናውን እየሰጡ ያገኘናቸዉ ፕሮፌሰር ኒርኦሪዮን እንደተናገሩት ስልጠናው በተለያዩ የአለማችን ሀገራት ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም  በኢትዮጱያ ግን የመጀመሪያ ነው ብለዋል፡፡ፕሮፌሰሩ አክለውም ይህ ስልጠና ለመምህራን የተሰጠው ተማሪዎቻቸውን ስለመሬት ሳይንስ፣ ስለ ከባቢ አየር፣ውሃ፣ ማዕድናትና ስለሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶች በአካባቢው የሚገኙ ቁሶችን ተጠቅመው በማስተማር ተጨባጭ እዉቀትን እንዲያገኙ ማድረግ እንዲቻል ብለዋል፡፡

 

በስልጠናዉ ሲሳተፉ ያገኘናቸዉ ዶ/ር ሀይሉ ሽፈራዉ ስለ ስልጠናው ሲናገሩ አሳታፊ የማስተማር ስነ-ዘዴን በመጠቀም ተማሪዎች ሳይንስን በቀላሉ እንዲረዱት ለማድረግ እንዲያስችል ሆኖ እንደቀረበ ተናግረዋል፡፡አክለውም ከስልጠናዉ በኋላም ወደ ተማሪዎች ወርዶ አሳታፊ በሆነ መልኩ ይተገበራል ብለዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ማበልፀጊያ ማዕከል (STEM CENTER) ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ ተገኘ በበኩላቸው ስልጠናው ከመምህራን በተጨማሪ በማዕከሉ ለሚማሩ ተማሪዎች በሙከራ ደረጃ በማጠቃለያው እንደሚሰጥ ጠቅሰው ይህም የተማሪዎችን ተነሳሽነት እንደሚጨምር ይታመናል ብለዋል፡፡

ሰልጣኞችም ከኢትዮጱያ ሳይንስ አካዳሚ ባለሙያዎች፣ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣የሳይንስ ኮሌጅ እና የመሬት አስተዳደር ትምህርት ቤት ፤እንዲሁም ከወሎ፣ ከጂማ፣ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ዱራሜ ከተማ ሀጋ ሞደል ትምህርት ቤት የተዉጣጡ መምህራንና ባለሙያዎች ናቸው፡፡

 

ከፌደራል እና ከክልል የተውጣጡ የከፍተኛ አመራሮች ግብረ-ሀይል ታህሳስ 17/ 2012 ዓ.ም. ከባህር ዳር ከተማ የሀይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ከወጣቶች እና ከክፍለ ከተማ ተወካዮች ጋር በመማር ማስተማሩ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ምክክር አደረጉ፡፡
=======================================================
በሙሉጌታ ዘለቀ
በተለያዩ ጊዜያት በዩኒቨርስቲዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪዎች እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ። የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም ከታህሳስ 13 ጀምሮ ከተማሪዎች፣ከዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ጋር ውይይት ሲያደርግ ቆይቷል። ዛሬም ከባህር ዳር ከተማ የሃይማኖት አባቶች፣ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከከተማው ወጣቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።
 
ውይይቱን ግብረ-ሀይሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው ይዞት የመጣውን ዋና ተልዕኮ በመናገር የመጀመሩት አቶ አማረ አለሙ የባህር ዳር ከተማ ም/ከንቲባና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ም/ሰብሳቢ ናቸው፡፡ አቶ አማረ እንዳሉት የባህር ዳር ከተማ ማህበረሰብ በተለያዩ አደረጃጀቶች በመሆን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ከቅበላ ጀምሮ ሰላምን በማስጠበቅ ቀላል የማይባል አሰተዋፆ ማበርከታቸውን ገልፀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችና የአካባቢው ህብረተሰብ ያላቸውን ሁለንተናዊ ቁርኝት ጠቅሰው፤ አሁን እንደ ሀገር ያጋጠመንን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላም እጦት ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆን መስራትና ቀደም ሲል የነበረውን ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት ወደ ቦታው መመለስ ይገባል ብለዋል፤ ለውጤታማነቱም ይህን መሰል ውይይት ማድረጋቸው ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በውይይቱም ላይ ህብረተሰቡ የዩኒቨርሲቲው ሰላም መሆን የከተማዋም ሰላም መሆኑን ገልፀው የዩኒቨርሲቲው ሰላም ሲታወክ የከተመዋም ገፅታም እንደሚደበዝዝ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ከአስር ሺህ በላይ ሰራተኞችና ከሃምሳ አራት ሺህ በላይ ተማሪዎችን የያዘ ግዙፍ ተቋም በመሆኑና በአንድም በሌላ ለከተማው ማህበረሰብ የኑሯቸው መሰረትም ስለሆነ ለሰላሙ መጠበቅ አጥብቀው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎችም በሚከሰቱ ወቅታዊ ችግሮች ሳይበገሩ ትምህርታቸውን መማር እንዳለባቸው እና ማንኛውም የባህር ዳር ከተማ ህብረተሰብ በሰላሙ ዙሪያ ከጎናቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተማሪዎች መካከል ተማሪ መስለው በብሄርና በቋንቋ ግጭትን ለመፍጠር ወረቀት የሚበትኑት አካላት ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ ከፅጥታ አካላትና ከከተማው ህብረተሰብ ውጭ ሰላልሆኑ ተይዘው ለህግ እንዲቀርቡና በግጭቱ ምክንያት ግቢውን ለቀው የወጡ ተማሪዎችንም በሚዲያ እንዲጠሩና እንደገና ምዝገባ ተካሂዶ ትምህርታቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ተሰብሳቢዎች ሀሳባቸውን ተናግረዋል፡፡ ካሁን በፊት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ “ባህር ዳር እንደቤቴ ” በሚል የተጀመረው እና በአሁኑ ሰዓት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በስፋት የተገበረውና ውጤታማ የሆነበት ከአማራ ክልል ውጭ የመጡ ተማሪዎችን ህብረተሰቡ እንደ ልጁ አድርጎ የሚንከባከብበት ፕሮግራም ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም ተማሪዎች በታላላቅ በዓላት ከባህር ዳር ነዋሪዎች ጋር ሲያከብሩ መቆየታቸውን አስታውሰው በዚህም ብቸኝነት ሳይሰማቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር የሆኑ ያህል እንዲሰማቸው ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ይህ በጎ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጋራ ሀሳብ የተያዘ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎችም የበኩላቸውን ለማድረግ ቃል ገብተዋል ፡፡
 
የገንዘብ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሃጂ ኢብሳ እንዳሉት ከአመታት በፊት ወደ ተማሩበት ዩኒቨርሲቲ በድጋሚ ስለመጡ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀው ህብረተሰቡ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ግጭቶች ሲከሰቱ በየኔነት ስሜት ከፀጥታ ሀይሉ እና ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በመሆን ተማሪዎችን በመምከርና በመገሰፅ የሰላም አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አቶ ሃጂ ቀጥለውም አሁን በተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እና ክልሎች እየታዩ ያሉት ጎሳን መሰረት ያደረጉ የሚመስሉት ግጭቶች ሰፊውን የኦሮሞን እና የአማራን ህዝብ ፈፅሞ እንደማይወክል ገልፀዋል፡፡ይልቁንም ጉዳዩ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት የተጠነሰሰ ሴራ ውጤት መሆኑን ጠቁመው የባህር ዳር ከተማ ህብረተሰብ ሴራውን እንደ ከዚህ ቀደሙ በተባበረ ክንድ እንዲያከሽፈው ጥሪ አድርገዋል፡፡
 
በእለቱ መድረኩ ላይ የነበሩት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኜ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት የኖረው በሀገር ሽማግሌዎች፣ በጸጥታ አካሉ እና በህብረተሰቡ ትልቅ እገዛ መሆኑን ጠቅሰው ላበረከቱት አስተዋፆ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በመቀጠልም ስለፖሊ ተማሪዎች መውጣት ከህብረተሰቡ ለቀረበው ጥያቄ ሲያብራሩ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች የሚመለከታቸውን የክልል ባለስልጣናት እና የሀገር ሽማግሌዎችን በመያዝም ውይይቶች እንደተደረጉ አንስተው ነገር ግን ተማሪዎች ትምህርት ሳይማሩ ለበርካታ ሳምንታት መቀለብ ስለማይቻልና ህጉም ስለማይፈቅድ ከብዙ ጥረት በኋላ ከአቅም በላይ ስለሆኑ ከግቢ መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ዶ/ር ፍሬው ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚገኙት ሁሉም ተማሪዎች ህጋዊ አገልግሎቶችን የሚያገኙት መማር ሲችሉ ብቻ መሆኑን ተናግረው የወጡ ተማሪዎችን ለመመለስና በተጠናከረ መልኩ ትምህርት ለማስጀመር የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ተሰብስቦ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ገልፀዋል፡፡
 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከሃኪም ወርቅነህ መላኩ በያን ሶሳይቲ ጋር በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ
****************************************************************************************
በሙሉጎጃምአንዱዓለም
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኮሌጁ ከሃኪም ወርቅነህ-መላኩበያን ሶሳይቲ ከተባለው በአሜሪካን ሃገር ተቀማጭነቱን ካደረገው የትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኮሌጁ የአካዳሚክና ምርምር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ገበየሁ እና የሶሳይቱ ተወካይ ዶ/ር ጌታቸው ፈለቀ ናቸው፡፡ በመርሃ-ግብሩ ላይ ሃኪም ወርቅነህ እና የህክምናው አባት ፕሮፌሰር እደማርያም ፀጋን በህክምናው ዘርፍ ያበከከቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ በሰፊው ተወስቶ ለወደፊት በህክምናው ሙያ የላቀ ውጤት አስመዝግበው ለሚመረቁ ተማሪዎች በፕሮፌሰር እደማርያም ስም ሽልማት እንደሚዘጋጅ በውይይቱ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በተጨማሪም ለተመረጡ ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንደሚሰጥ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሳተላይት ስታመጥቅ የSTEM ተማሪዎች በአንድ ላይ ሆነው ተመልክተዋል

ኢትዮጵያ ኢቲ.አር.ኤስ.ኤስ አንድ የተሰኘ የመጀመሪያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ስታመጥቅ  ከእንጦጦ ስፔስ ሳይንስ የተካሄደውን የቀጥታ ስርጭት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከል ተማሪዎች አንድ ላይ አዳራሽ ውስጥ በመገኘት ተከታትለዋል፡፡

በኩነቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ኢትዮጵያ በታሪኳ በዚህ ከፍታ እንደነበረች እንደሚታመን ገልፀው ጊዜ ወደ ኋላ ሲተረተር ሀገራችን በመስኩ እውቀት ቀዳሚ የነበረች መሆኗን ጠቋሚ ነው ሲሉ የነገ ተስፋ ለሆኑት ታዳጊ ተማሪዎች አነቃቂ ንግግር አድርገዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ወደ ኃላ ትመለሰ እንጂ ወደ ነበረችበት ከፍታ ለመመለስ አቅም እንዳላት ጥሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ከዚህ የተገኛችሁ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተማሪዎች ኢትዮጵያ ወደፊት በራሷ አቅም ለምታመጥቀው ሳተላይት የስራው ተሳታፊ ለመሆን እንደምትችሉ ተስፋ አለኝ ሲሉ እምነታቸውን ገልፀው የኛም እገዛ እንደማይለያችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ንግግራቸውን ቋጭተዋል፡፡

በባሕር ዳር ዩንቨርስቲ ዋሸራ ስፔስ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፊሰር ፀጋየ ካሳ በበኩላቸው የመጠቀችው ሳተላይት 700 ሜትር ላይ ሁና በኢትዮጵያ ያለውን የተለያዩ የመሬት እንቅስቃሴዎች ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፎቶ ግራፍ እያነሳች መልዕክት ትልካለች፤ በተገጠሙላትም ሴንሰሮች 13 ሜትር በ13 ሜትር የመሬት ምልከታ ታደርጋለች ብለዋል፡፡ ከእንጦጦ ስፔስ ማዕከልም ባለሙያዎች ሞገድ ይልካሉ ከዛም ይቀበላሉ ስለዚህ ቁጥጥሩ በኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ይከናወናል ብለዋል፡፡

BDU in collaboration with  four other international universities holds GIS 4 East Africa Summer School program

GIS 4 East Africa Summer School hosted by Geospatial Data & Technology Center (GDTC) of Bahir Dar University was concluded on 15th of December 2019. The summer school, which was held from December 5-15, 2019, was sponsored by DAAD in collaboration with Bahir Dar University, Juba National University, Beuth University of Applied Sciences Berlin, Université Evangeliqueen Afrique and El Neleen University. In the summer school, 35 GIS experts from Sudan, South Sudan, D.R. of Congo, Germany and Ethiopia have participated. The objective of the summer school was to capacitate GIS experts of the above mentioned nations to apply GIS for decision support. The summer school also served as a platform to strengthen the North-South and South-South relationships between the participating countries.

Geospatial Data & Technology Center (GDTC), BDU provides Geographic Information System (GIS) Training for Natural Resource Management experts

=================================================================================

Geospatial Data & Technology Center (GDTC) in collaboration with Vice President for Research & Community Service Office of Bahir Dar University is offering a GIS training for twenty-three Natural Resource Management experts working at Zonal and Woreda (District) level. The training is a tailor-made training designed to enable Natural Resource Management experts to use GIS in their day to day activities.

The ever rising human population is depleting natural resources in a range of time making resource management a prior agenda for concerned bodies. A lot of management practices have so far been advanced in this regard. With the current trend in the advancement in the field of information technology, natural resource managers have now laid a lot of emphasis on the use of remote sensing and GIS technologies in the management of natural resources. These technologies provide a platform based on which managers can generate informative data and information that can be used to make sound decisions for sustainable development.

It is with the above assertion that the Geospatial Data & Technology Center (GDTC) office arranged the current training. The content of the training includes introduction to GIS, working with ArcGIS, data extraction from Google Earth, Data collection using GPS and displaying in ArcGIS, spatial and non-spatial data integration and watershed delineation for development planning. At the end of the training, it is expected that the trainees will be able to appreciate the capability of GIS technology in natural resource management. They will also be able to use GIS technology in their day to day activity.

Bahir Dar University, BDU, is currently engaged on important research activities with a goal to be one of the Top 10 Research Universities in Africa by 2025. With this mission the university is working on the quality of its research along with increasing research visibility to the greater world. For the last two years the Research and Community Service Vice President Office has been working to support research activities with a Current Research Information System to facilitate, preserve, disseminate, reach the academic society, and identify better collaboration and career opportunities for researchers.

In the framework of the VLIR-UOS project and in collaboration with 4Science, www.4science.it, an organization supporting DSpace-CRIS worldwide, the ICT Directorate of BDU, a core component  engaged in supporting teaching, learning, the library, and business and administration activities of the university, worked to gather with the Research and Community Service Office on implementing the Research Information Management System – RIMS for the university’s research ecosystem as a whole.

Our partners from VLIR-UOS: 4Science, Ghent University, and IRD-Institut de recherche pour le développement, have been working with the ICT Directorate and RCS Office on refining the BDU’s Open Access Policy for RIMS in December 2019.  In the near feature the Research Information Management System - RIMS will be launched to play a relevant role for Bahir Dar University.  

Pages