Latest News

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአፋር  ክልል በአሸባሪው ትህነግ ጉዳት ለደረሰባቸውና ለተፈናቀሉ  ወገኖች  የምግብ ዱቄት ድጋፍ  አደረገ።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በችግር ላይ ለሚገኙ የአፋር ወገኖቻችን ከ830 ሺህ  ብር  በላይ  የሚያወጣ  200  ኩንታል  የምግብ  ዱቄት  ድጋፍ አደረገ ፡፡

የምግብ ዱቄቱን ርክክብ የፈፀሙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ግንኙነት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ታደሰ አክሎግ  እንዳሉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል ውስጥ እንደሚገኝ የፌዴራል ተቋም ያለውን ውስን ሀብት በማብቃቃት በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ጉዳት ለደረሰባቸው ለጀግናው እና የሰው ዘር መገኛ ለሆነው ለአፋር ህዝብ ተቆርቋሪነቱን ለመግለፅ ከ830 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ 200 ኩንታል የምግብ ዱቄት በመያዝ ሰመራ መገኘታቸውን ጠቅሰው ድጋፉ ለወደፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ 

 

ተጎጅዎች በከፍተኛ ችግር ያሉ በመሆኑ ሌሎች የፌዴራልም ሆነ የክልል ተቋማት የችግሩን ስፋት በማየት  በጦር ሜዳ ግንባር ከሚያደርገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በመደገፍ  በኩል የራሳቸውን አስተዋጾ ማድረግ እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

 

ድጋፉን የተረከቡት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አቡበከር ያሲን እንዳሉት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከውስጥም ሆነ  ከውጭ  በሚመነጩ ችግሮች  ዜጎች ላልተገባ ሞትና መፈናቀል እየተዳረጉ በመሆኑ;  አሁን እያደረግነው ያለውን የህልውና ጦርነት ለማሸነፍ እና ሀገራዊ አንድነታችን ለመጠበቅ የውስጥ አንድነታችን ማጠናከር  እና መተሳሰብ እንደሚገባ አውስተው; የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን የሕዝብ አንድነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ስራዎችን  መስራት እንዳለባቸው አቶ አቡበከር ጠቁመዋል፡፡  

የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ 607,500 ብር የሚያወጣ 100 ኩንታል ነጭ ዱቄትና 50 ኩንታል መኮሮኒ በተመሳሳይ ቀን በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ የአፋር ወገኖች ድጋፍ አበርክቷል ።

በመጨረሻም የምግብ ድጋፍ ላደረጉ ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  እና ለደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የክልሉ መለያ የሆነውን ጊሌና የምስክር ወረቀት ሽልማትን የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ከሆኑት ዶ/ር ሙሀመድ ዑስማን እጅ ተረክበዋል፡፡

በሙሉጌታ ዘለቀ

 

ከብርጋዴል ጀነራል ካሳዮ ጨመዳ ህይወት ስለ ኢትዮጵያ

 

ብርጋዴል ጀነራል ካሳዮ ጨመዳ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞችና አመራር አካለት ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የህይወት ልምዳቸው፣ ለሀገራቸው ያበረከቱት እና ስለ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ያላቸው ጥልቅ ፍቅር በውይይቱ ተወስቷል፡፡ ጀነራሉ ለውይይት ባቀረቡት ንግግር ብዙ ርዕሰ ጉዳዮችን የዳሰሱ ሲሆን ምዕራባዊያኑ በሀገራችን ላይ ስለያዙት የተሳሳተ አቋም፣የወቅቱ ወራሪዎች የስግብግብነትና ዘረኝነት በሽታ የሚያስፋፉ  ስለመሆናቸው፣ ስለ ህገ-መንግስቱ እና ሌሎች ጉዳዮች አንስተዋል፡፡

 

በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አገልግሎት ዲን ምኒችል ግታው(ዶ/ር) ብርጋዴል ጀነራል ካሳዮ ጨመዳ በዘመን ቅብብሎሽ ውስጥ በኢትዮጵያዊነት ማማ ላይ የኖሩ ለመውረድም እምቢ አሻፈረኝ ያሉ ትልቁ የኦሮሞ ህዝብ ያፈራቸው ታላቅ ኢትዮጵያዊ ናቸው ብለዋል፡፡ ብ/ጄ ካሳዮ ጨመዳ በዘመኑ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ቢያመጡም በነበራቸው የሀገር ፍቅር ምክንያት ሀረር ጦር ትምህርት ቤትን በመቀላቀል ለ3 ዓመት የተሰጠውን ስልጠና በብቃት በማጠናቀቅ በምክትል ሻለቃ ማዕረግ ተመርቀዋል፡፡ ከዚያም የ16 ኛው ሰንጥቅ ክፍለ ጦርን መስርተው ትልቅ ውለታ የዋሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ የታንከኛ ሙያ በሀገር ውስጥ በእስራኤሎች ለሁለት ዓመት ሰልጥነዋል፡፡ በሌላ መንገድ ለከፍተኛ ታንክ ስልጠና ወደ አሜሪካ በመጓዝ በከፍተኛ ውጤት ተምረው አጠናቀዋል፡፡ እንዲሁም በምስራቅ፣ በምዕራብ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተካሄደው ውጊያዎች ላይ በከፍተኛ የሀገር ስሜት ወኔና ጀግንነት ተሳትፈዋል፡፡በቀድሞው ህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ የሁለተኛ ሜዳሊያ ተሸላሚ ናቸው፡፡ በተካሄዱ ውጊያዎች ላይ ሲያደርጉት በነበረው ተጋድሎ ቆስለዋል ደምተዋል በዚህም የቁስለኛ እና የዘመቻ ተሳትፎ አርማ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በሌላ መንገድ በሀሰት ተወንጅለው ለረጅም ዓመታት በእስር ተሰቃይተዋል ለሚወዷት ሀገራቸውም ዋጋ ከፍለዋል፡፡ በአሁኑ ስዓት በጡረታ የሚገኙ ቢሆኑም አገራቸው ባገር አፍራሾች ስትነካ፤ ጊዜ ሳይገድባቸው የነበራቸውን ልምድ እያካፈሉ አገራቸውን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ብ/ጄ ካሳዮ ጨመዳ  ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ጠርተው የማይጠግቡ ታላቅ የአገር ባለውለታና የህዝብ እውነተኛ ልጅ ናቸው ብለዋል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ አቶ ቻላቸው ታረቀኝ በበኩላቸው ብርጋዴል ጀነራል ካሳዮ ጨመዳ ሲነሩ ፈረንጆቹ ለምን ኢትዮጵያን ጠመዷት፣ ኢትዮጵያ የጥበብ አገር መሆኗን ነግረውናል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ ሀይማኖት መኖሩ ለውጭ ሀይሎች አለመመቸት አስረድተውናል፡፡ ሌላው አውሮፓውያን የተሻለ ያውቃል የሚሉትን ምሁራን ወደ ውጪ በማስኮብለል አገሪቱ ድሃ ሆና እንድትቀር አድርገዋል፡፡ እንዲሁም በሴፍት ኔት ፕሮግራማቸው ህዝቡ ልመናን እንዲለማመድ ሰርተዋል በማለት በኮንጎ ያለውን ሁኔታ በምሳሌነት ዳሰዋል፡፡  በተጨማሪም ህገ መንግስቱ ብዙ ችግር ያለበት በመሆኑ መሻሻል እንዳለበት ጠቅሰው ለውይይት በሚመች መልኩ አቅርበዋል፡፡ 

በዮኒቨርሲቲያችን የሚገኙ የተለያዩ ሰራተኞች እና አመራር አካላትም ብርጋዴል ጄነራል ካሳዮ ጨመዳ በወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ ላይ ተመስርተው በሰጡት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ በማንሳት ተወያይተዋል፡፡ 

 

Bahir Dar University, Institute of Technology gives hands-on training

The ICT4D research centre under Institute of Technology of Bahir Dar University together with Targeted Institute of Technology gave training titled “Advanced Web Design and Development/ full-stack” virtually.

The topics covered in the training include Basics of HTML፣ CSS፣ Web development with Wordpress፣ Introduction of Databases with MySQL፣ Javascript፣ Node.js. The training was hands-on in type and the trainees were working on some feasible projects as part of the training.

Dr Esubalew Alemneh, Director of the centre, presented Certificates for seventeen of the trainees with full attendance.

https://www.facebook.com/bitpoly/posts/1416461812088318

College of Medicine and Health Sciences organizes training on Data Management, Data Analysis, and Scientific Paper Writing for residents. https://www.facebook.com/cmhsbdu/posts/1834897723378471

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማኔጅሜንት አባላት የ2013 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ከመስከረም 11-12/2014 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡ በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር አበራ ከጪ በ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዋና ዋና ተግባራት ላይ አቅጣጫ በመስጠት ተጠናቋል ፡፡

Bahir Dar University, The Ethiopian Textile and Fashion Technology Institute management members held a two-day (September 21-22, 2021) long performance evaluation of the Academic year 2020/21.

The meeting is concluded with the directions given by Dr. Abera Kechi, Scientific Director of the Institute, on the major activities for the coming Academic year 2021/22.

ፕሮፌሰር እዩዓለም ተሞክሯቸውን አካፈሉ

Alliance for Research, Innovation, and Education ( AfRIM ) የተሰኘውና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አቅም  ለማጎልበት የተመሰረተው የዓለምአቀፍ ሳይንቲስቶች፣ ተመራማሪዎች ጥምረት መሪ ቡድን አባል እና የ Elizabeth City State University ፕሮፌሰር እዩዓለም አበበ በአውሮፓና አሜሪካን ኢንስቲትዩቶችና ስርዓቶች፤ የዩኒቨርስቲያችን ምሁራንና አካዳሚክ አመራሮች እንዲሁም የከፍተኛ አመራር አባላት በተገኙበት የካበተ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

የውይይቱ ዓላማ እንደ ምርምር ዩኒቨርሲቲ ወደፊት ለመጓዝ ምን ነገሮች ላይ ብንሰራ ጥሩ እንደሚሆንና ሙያዊ ጉዳዮች ላይ እንዴት መተጋገዝ እንደሚቻል የሀሳብ ልውውጥ ማድረግ ነው፡፡  

በውይይቱ መክፈቻ የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጅክ ኮሙኒኬሽን ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ AfRIE ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ከመሆኑም በላይ ዩኒቨርሲቲያችንን እንደምርምር ዩኒቨርሲቲ አሁን ከደረሰበት የእድገት ደረጃ በመነሳት ተቋሙን ወደታለመለት ግብ ለመድረስ ምን አይነት ሙያዊ ድጋፍ እንደምንፈልግ ደጋግሞ በመጠየቅ ከሌላው የAfRIE መሪ ከሆኑት መካከል ከዶ/ር ዮናስ ግዛው ጋር ከወራት በፊት ውይይት መደረጉን አውስተዋል፡፡

ኃላፊው አያይዘው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በAfRIE ተግባራዊ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ሁለት ዙር የ Grant Writing Workshop በማካሄድ ለበርካቶች የምርምር አቅም ፈጠራ ተጨባጭ ስራ እየሰራ የሚገኝና ስልጠናውን ተከትሎም ለተወሰኑ ስልጣኞች የሜንተሪንግ ስራ እየሰራ ያለ ቡድን ነው ብለዋል፡፡

ተሳታፊዎችም እንደ ምርምር ተቋም የተሻለ ለመሆን ምን ይቀረናል፣ ወደ ምርምር የሚያስገባው ስልጠና ምን መልክ ይኑረው፣ በዩኒቨርስቲው ምን አይነት ስርዓት ቢዘረጋ ነው ተመራማሪው ምርምሩን ብቻ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ የሚሆነው፣ ማህበረሰቡ ለትምህርት (ምርምር) ያለውን ግንዛቤ እንዴት እናሳድግ፣ ምርምርን የችግር መውጫ መንገድ ከማድረግ ባለፈ፤እንዴት ነው እውነተኛ ተመራማሪ መሆን የሚቻለው? የሚሉት ጥያቄዎች አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

 

የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪ የመፅሀፍ ልገሳ አደረጉ
========================
‹‹ፀሐይ›› በሚል ርዕስ በዘለዓለም አንዳርጌ (ካፒቴን) ተደርሶ የኢትዮጵያን አቪየሽን አጀማመር የሚተርኩ፤ ግምታቸው 50 ሺ ብር በላይ የሚሆን 300 መጽሀፍትን የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪ የአቪየሽን ግሩፕ መስራች አቶ ዮናታል መንክር ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቤተ- መጻሕፍት አስረክበዋል፡፡
አቶ ዮናታል በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ‹‹መንክር›› የጥናት ፓርክ በማቋቋም ተማሪዎች ሀሳብ እንዲለዋወጡ፣ የህይወት ልምድ እንዲያደርጉ ከጓደኞቻቸው ጋር መስራታቸውን አስታውሰው፤ ብዙ ሰው ሀሳብ ሊያመጣ ይችላል የሚቀበለው ለም መሬት ነው ወይስ ጭንጫ ነው ብሎ መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ዩኒቨርሲቲውም መጽሀፉን ለማስረከብ ሀሳቡን ሳቀርብ ሀሳቡን ስለተቀበለኝ አመሰግናለሁ ብለዋል ፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በመክፈቻ ንግግራቸው ቤተ መጽሀፍታችን በአገር አቀፍ ደረጃ በዲጅታል ላይብራሪ የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው መጽሀፍቱ ወደ ዩኒቨርሲቲ መምጣታቸው የመላው ኢትዮጵያ ስብስብ የሆነው የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እያነበበ ብሎም እየተመራመረ የሚጠቀምበት ይሆናል ብለዋል፡፡
‹‹በዓለም የአቪየሽን ታሪክ አብራሪነት የነጮች ሙያ ብቻ ተደርጎ በሚቆጠርበት ዘመን፣ የራሱን አብራሪዎች በማፍራት ረገድ ኢትዮጵያ ከዓለም በግንባር ቀደምትንት ከሚቆጠሩት ጥቂት አገሮች ተርታ የምትመደብ መሆኑን ከዚህ መጽሀፍ ታሪክ መረዳት ይቻላል፡፡ በተለይ ‹‹ፀሐይ›› ስለተባለችው አውሮፕላን እዚሁ አገር መሠራት እና አውሮፕላኗም በስደት ኢጣሊያ አገር ሙዚየም ውስጥ ስለመገኘቷ የሚያሳየው ክፍል፣ ስለምን ሥልጣኔያችን እንዳጀማመራችን ሳይሆን ቀረ አስብሎ የሚያስቆጭ ነው፡፡ ካልተነገረለት የአቪየሽን ታሪካችን በተጨማሪ፣ ከ1920ዎቹ መጀመሪያ አንስቶ የተከናወኑ እና የተከሰቱ ሌሎች ታሪካዊ ሁነቶችንም በጥናት ላይ ተመስርቶ መተረኩን በመጽሀፉ ሽፋን ተፅፎ ይገኛል፡፡
በርክክብ ስነ ስርዓቱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቤተ መጽሀፍት ዳይሬክቶሬት እና የኢንፎርሜሽን ስትራቴጅክ ኮሚኒኬሽን ም/ፐሬዝዳንት ተገኝተዋል፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ይህን አርአያነት ያለው ተግባር ያደንቃል!

የወታደራዊ ሰልጣኞች ምረቃ

መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና የወሰዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በዩኒቨርሲቲው የስፖርት አካዳሚ ስታዲየም ፕሬዘዳንቱን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የምረቃ ስነ- ስርዓቱ ተካሂዷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ የስልጠናው ዋና ዓላማ ህብረተሰቡንና ንብረቱን ከተደቀነበት የህልውና አደጋ ለመጠበቅ ታልሞ እንጂ ሌላ ተልኮ እንደሌለው ገልፀው አገርንና ህዝብን ለመጠበቅ የትምህርት ደረጃ ገደብ የሌለው መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ በማስከተል የውጩ ዓለም ተሞክሮ ከፕሮፌሰርነት እስከ ተራው ህዝብ ድረስ ለውትድርና ዝግጁ ሆነው እንደሚጠብቁ አውስተው ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ለውትድርና እራሱን ቢያዘጋጅ ከጥቃት መከላከል እንደሚችል ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጲያ አገራችን የማንንም አገር መብት የማትደፍርና ከነኳት ግን ጥግ ድረስ ወራሪ ጠላትን የምታንበረክክ መሆኗን ዓለም እንደሚመሰክር አስገንዝበው ሰልጣኞች ከስልጠናው መልስ መተኛት እንደሌለባቸውና አካባቢያቸውን በንቃት መጠበቅ እንደሚገባቸው ፕሬዘዳንቱ አሳስበዋል፡፡

የሰልጣኞች ብዛት 425 ሲሆን ከወታደራዊ አሰላለፍ እስከ የጨበጣ ውጊያ ድረስ ያለውን ሂደት ለታዳሚዎች አሳይተዋል፡፡ በመጨረሻም ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ያቀረቡ ሲሆን ለአሰልጣኞችና ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት በአመራሮች ተሰጥቷል፡፡

በሙሉጎጃም አንዱዓለም  

 

የስራ ተኮር የምክር አገልግሎት ስልጠና ተሰጠ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ለ2013 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛው መርሃ ግብር ተመራቂ ለሆኑ 3250 ተማሪዎች ከውጤታማ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ከመስከረም 3-7/2014 ዓ.ም ድረስ TOT በወሰዱ አሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

 

ስልጠናው ግለ ግምገማና የስራ እና የተለያዩ የስራ መስኮችን ማጤን/መዳሰስ፣ ከሰዎች ጋር ተግባብቶ መስራትና ችግርን የመፍታት ክህሎት፣ ስራ የመፍጠርና የመፈለግ ክህሎት፣ የተለያዩ የሙያ ዘርፎችን መዳሰስ፣ የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ (CV Preparation) ማዘጋጀት፣የስራ ማመልከቻዎችን (Cover letter Preparation) ማዘጋጀት፣ በሚሉ ይዘቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የተጠናቀቀ መሆኑን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ ገልፀዋል፡፡

 

በስልጠናው ወቅት ያገኘናቸው የስራ ተኮር የምክር አገልግሎት ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ዮርዳኖስ ይበልጣል እንደገለፁት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የሙያ ማበልፀጊያ ማእከል የዩኒቨርሲቲውን ራዕይና ተልዕኮ መሰረት በማድረግ ተማሪዎች ተመርቀው ሲወጡ በሙያቸው ተወዳዳሪ፤ ስራ ፈጣሪ፤ የስራ ቅጥር እድልን ማሳደግ ፤ በስራ ቅጥር ውድድር አሸናፊ እንዲሆኑ ፤ በህይዎታቸውና በስራ አለም የሚገጥማቸውን ችግሮች የመፍታት ክህሎት ማዳበር እና ሙያዊ ስነ ምግባር ያላቸው እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የሙያ ማበልፀጊያ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ይህንንም መሰረት በማድረግ ማዕከሉ፡ ራስን የመፈተሽና የተለያዩ የስራ መስኮችን ማጤን፤ የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠናዎችን፡ የገበያ ተወዳዳሪነት ክህሎት ስልጠናዎችን፤ የሙያ ስነ ምግባር ስልጠናዎችን በመስጠትና የስራ እድሎችንም በማመቻቸት እየሰራ ይገኛል ብለዋል ፡፡

 

በስነ ልቦና ትምህርት ክፍል መምህር መሰረት አያሌው በበኩላቸው የስልጠናው አላማ ተመራቂዎቻችን በገበያው አለም ተወዳዳሪ ሆነው ወደ ስራ አለም እንዲገቡ እና ስራ መፍጠር የሚያስችል የስራ መፈለግ እና የስራ ፈጠራ ስልጠና ነው ፡፡ ትኩረቱም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ብዙም ቦታ ያልተሰጠው ሆኖ ማለትም የግል ታሪካቸውን እንዴት ማዘጋጀት ይችላሉ፣ ቃለ መጠይቆችን እንዴት ይመልሳሉ የሚሉ ናቸው፡፡ አንደኛው እራስን ማወቅ ሌሎችን መረዳት ወይም ዕውቀታቸውን መለየት እና ከነሱ እውቀት፣ ፍላጎት ጋር የሚሄዱትን ፈልጎ ለዚያ መዘጋጀት ሲሆን የተመረቁበት ትምህርት ስራው የማይገናኝ ከሆነ በነሱ ፍላጎት የሚሆን ስራ መፍጠር የሚያስችል ስልጠና ነው ብለዋል፡፡  

 

Pages