የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ አካዳሚክ ካውንስል ስብሰባ ቃለ ጉባኤ

ቦታ፡ የሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ ዲን ቢሮ

ሰዓት፡ 4፡00- 5:00

ቀን፡ 08/02/2006

 

በስብሰባው የተገኙ አባላት

1.

ዶ/ር ስዩም ተሾመ

የሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ ዲን

ሰብሳቢ

2.

ዶ/ር ሙሉጌታ ተካ

የምርምርና፣ድኀረ ምረቃ ማኀበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ

አባል

3.

ዶ/ር በቀለ ብርሃኔ

የፕሮግራም ማኔጀር ተወካይ

አባል

4.

አቶ ተመስገን በየነ

የፎክሎር ýሮግራም አስተባባሪ

አባል

5.

ወ/ሮ ሰሎሜ ዘውዳለም

የአማርኛ ýሮግራም አስተባባሪ

አባል

6.

ዶ/ር ብርሃኑ ስመኝ

የእንግሊዝኛ ýሮግራም አስተባባሪ

አባል

7.

አቶ ተስፋዬ ተሾመ

የደንበኞች አገልግሎት አስተባባሪ እና የትምህርት አማካሪ

አባል

8.

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን

የጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽንስ ýሮግራም አስተባባሪ

አባልና የዕለቱ ፀሐፊ

 

አጀንዳዎች

  1. 1.ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ
  2. 2.የተማሪዎች ጉዳይ
  3. 3.የመምህራን ጉዳይ
  1. 1.ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ

ሂፋ/አካ/04/2006 እና ሂፋ/አካ/05/2ዐ06 በሙሉ ድምፅ ፀድቋል

  1. 2.የተማሪዎች ጉዳይ

2.1ዝውውር

ሰለሞን አቡዬ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነፁሁፍ አማርኛ ፕሮግራም የአንደኛ ዓመት ተማሪ በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በ2005 ተመዝግቦ በነበረበት የጤና ችግር ምክንያት ያልተማረ እና ምንም አይነት ውጤት ያልተመዘገበለት መሆኑን ኮሌጁ ገልጾ ለባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እንዲቀበለው በጠየቀው መሠረት ካውንስሉ ተወያይቶ ልጁ አይነስውር በመሆኑና በአካባቢው ሆኖ መረዳት ስላለበት በዚህ ዓመት ተመዝግቦ ትምህርቱን እንዲቀጥል ወስኗል (አባሪ አንድን ይመልከቱ)፡፡

2.2. መልሶ ቅበላ

ተማሪ የሱፍ አደም መሀመድ የተባለ የ2ኛ አመት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪ ፣ሰአዳ ሀሰን ፎክሎር ፕሮግራም የ3ኛ አመት ተማሪ እና የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ፕሮግራም አማርኛ ተማሪ ተሚማ ሁሴን የተባሉ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ማካሄድ የሚከለከለውን አንቀጽ በመቃወም በህጉ የፀደቀውን መተዳደሪያ ደንብ በመጣስ በራሣቸው ፈቃድ ትምህርታቸውን አቋርጠው መሄዳቸውን በመጥቀስ ዩኒቨርሲቲውን ወደፊት ተመሣሣይ ጥፋት ከፈፀሙ በራሣቸው ፈቃድ ዩኒቨርሲቲውን እንደለቀቁ እንደሚቆጠር በፊርማቸው በማረጋገጥ ዩኒቨርሲቲውን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ካውንስሉም የቀረበውን መረጃ በአፅንኦት በማየት ምዝገባው እንዲፈቀድላቸው ወስኗል (አባሪ ሁለትን ይመልከቱ)፡፡

2.3.   የመመረቂያ ፅሁፍ የመስሪያ ጊዜ ይራዘምልኝ ጥያቄ

መንበሩ ገላይ የተባለ TEFL (MEd) የድህረ ምረቃ የExtention ተማሪ ከአሁን በፊት በስህተት ተመዝግቤ የጥናታዊ ፅሁፌ በክረምት መረጃ መሠብሰብ ስላልቻልኩ ለሶስተኛ ጊዜ የመስሪያ ጊዜ ይራዘምልኝ በማለት ጠይቋል፡፡ ካውንስሉም ምንም እንኳ ለሶስተኛ ጊዜ ህጉ ባይፈቅድም ከአሁን በፊት የተመዘገበው አክቲቭ ተማሪ ካልሆነ መቀጠል የማይችል በመሆኑና የጥናቱ አማካሪ ጥናቱ በክረምት የማይሰራ መሆኑን አሥተያየት የሰጡበት መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለመጨረሻ ጊዜ እንዲፈቀድለት ወስኗል (አባሪ ሦስትን ይመልከቱ)፡፡

2.2ኮርስ Add የማድረግ ጥያቄ

የሶስተኛ ዓመት የጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽንስ ተማሪዎች አንደኛ ዓመት በነበሩበት ጊዜ በካሪኩለም ችግር ምክንያት በተከታታይ መሠጠት የነበረባቸው ኮርሶች በአንድ ላይ በመመዝገባቸው ማለትም (Advanced Writing Skills) እና Basic Writing Skills በወቅቱ Basic Writing Skills ብቻ ወስደው Advanced Writing Skills drop እንዲያደርጉ በሂፋ/አኮ/29/2004 ተወስኖላቸዋል፡፡ ነገር ግን Advanced Writing Skills ኮርስ ስላልወሰዱ ተመዝግበው በአንደኛው ወሰነ ትምህርት እንዲወስዱ በጠየቁት መሠረት ኮርሱን ሲመዘገቡ አጠቃላይ CP 36 ስለሚሆንና ከሚፈቀደው በላይ ሆኖ ስለተገኘ በሚቀጥለው ወሰነ ትምህርት ተመዝግበው እንዲወስዱ ተወስኗል፡፡

  1. 3.የመምህራን ጉዳይ

3.1የትምህርት ጊዜ ይራዘምልኝ ጥያቄ

የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ጽሑፍ የስራ ባልደረባ የሆኑት አቶ ቸሬ መሥፍን እና የጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽንስ ፕሮግራም ባልደረባ የሆኑት አቶ መሥፍን አወቀ የPhD የት/ት ጊዜ እንዲራዘምላቸው ካውንስሉን ጠይቀዋል፡፡ ካውንስሉም የቀረቡት ማስረጃ በሚገባ በማጤን የት/ት ጊዜው በአንድ ወሰነ ትምህርት እንዲራዘምላቸው ፈቅዷል (አባሪ አራትን ይመልከቱ)፡፡

3.2ነፃ የትምህርት ዕድል ይፈቀድልኝ ጥያቄ

አቶ ያሬድ ፀጋዬ በእንግሊዝኛ ፕሮግራም በTechnical ረዳትነት ተቀጥረው እየሰሩ መገኘታቸውን ጠቅሰው በግላቸው በማታው መርሃ ግብር Electrical Engineering ለመማር ስለፈለጉ የነፃ ት/ት ዕድል እንዲፈቀድላቸው ካውንስሉን ጠይቀዋል፡፡ ካውንስሉም ጥያቄያቸውን በስፋት ከተወያየ በኋላ የጠየቁትን ትምህርት መስክ ቢማሩ አሁን ለሚሰሩበት ሙያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላለውና አመልካቹ ጠንካራ ሠራተኛ በመሆናቸው የጠየቁትን ትምህርት እንዲማሩ በመወሰን ፋኩልቲው ለሚመለከተው ክፍል እንዲያሳውቅ ወስኗል (አባሪ አምስትን ይመልከቱ)፡፡

3.3የዲስፒሊን ኮሚቴ አባል መምረጥ

ዶ/ር በቀለ በ2005 የት/ት ዘመን ፋኩልቲውን ወክለው የዲስፒሊን ኮሚቴ ሆነው ሠርተው የስራ ጊዚያቸውን ስላጠናቀቁ በዚህ አመት ሌላ ሰው እንዲመረጥ የዋናው ግቢ የተማሪዎች አገልግሎት በየጠቀው መሠረት ካውንስሉ የፎክሎር ፕሮግራም ባልደረባ የሆኑትን አቶ ሞገስ ሚካኤል የፋኩልቲው የዲስፒሊን ኮሚቴ አባል እንዲሆኑ ወስኗል፡፡

3.4እገዳ ይነሳልኝ ጥያቄ

የጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽንስ ፕሮግራም ባልደረባ የሆኑት አቶ ልኡል ተ/ስላሴ ከአሁን በፊት ከማስተማር ስራ ታግደው የነበሩ መሆናቸውን ጠቅሰው ጥፋቴን አርሜ የሚጠበቅብኝን ለማድረግ ዝግጁ ስለሆንኩ ወደ ማስተማር ሥራዬ እንድመለስና የተማርኩት ት/ት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ስለሆነ ወደ እንግሊዝኛ ፕሮግራም ተዛውሬ ብሰራ የበለጠ ውጤታማ ስለምሆን ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ጽሑፍ ፕሮግራም እንድዛወር የሚል ጥያቄ ለካውንስሉ አቅርበዋል (ለዝርዝሩ አባሪ ስድስትን ይመልከቱ)፡፡ ካውንስሉም የመምህሩን ጥያቄ በሚገባ ከተወያየ በኋላ ካቀረቡት ማስረጃ አኳያ ለጊዜው ማለትም ለአንድ ወሰነ ት/ት ለአንድ ክፍል Communicative English Skills ኮርስ እያስተማሩ ለውጣቸው እንዲታይ እና ቋሚ ውሳኔም በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ለመስጠት ወስኗል፡፡

 

ማሳሰቢያ፡-

  1. vየድህረ ምረቃ አካዳሚክ አማካሪዎች ተማሪዎችን ጉዳይ በደንብ እንዲከታተሉ እና እንዲያማክሩ
  2. vኮርስ በተለያየ ምክንያት ያልጀመሩ ከፋኩልቲያችን ውጭ የሚመጡ መምህራን ካሉ ኮርስ እንዲጀምሩ እንዲደረግ ዲኑ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

ስብሰባው በ6 ሰዓት ተጠናቋል፡፡

               ሰብሳቢ                                         ፀሐፊ

           …………………..                               …………………….

 

 

ሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ አካዳሚክ ካውንስል ስብሰባ ቃለ ጉባኤ

 

 

 

ቦታ፡ ከፋኩልቲው ዲን ጽ/ቤት

 

ሰዓት፡ 4፡00

 

ቀን፡ 03/02/2006

 

 

 

1.

ዶ/ር ስዩም ተሾመ

የሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ ዲን

ሰብሳቢ

2.

ዶ/ር ሙሉጌታ ተካ

የምርምርና፣ድኀረ ምረቃ ማኀበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ

አባል

3.

ዶ/ር በቀለ ብርሃኔ

የፕሮግራም ማኔጀር ተወካይ

አባል

4.

አቶ ተመስገን በየነ

የፎክሎር ýሮግራም አስተባባሪ

አባል

5.

ወ/ሮ ሰሎሜ ዘውዳለም

የአማርኛ ýሮግራም አስተባባሪ

አባል

6.

ዶ/ር ብርሃኑ ስመኝ

የእንግሊዝኛ ýሮግራም አስተባባሪ

አባል

7.

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን

የጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽንስ ፕሮግራም አስተባባሪ

አባል

8.

አቶ ተስፋዬ ተሾመ

የደንበኞች አገልግሎት አስተባባሪ እና የትምህርት አማካሪ

አባልና የእለቱ ፀሐፊ

 

 

 

 

 

 

 

 

በስብሰባው ያልተገኙ አባላት                                             ምክንያት

የለም

አጀንዳ

 

ተማሪ ጉዳይ- የፕሮቤሽን ጥያቄ

በፋኩልቲያችን በተለያዩ ፕሮግራሞች በ2005 ዓ.ም. የሁለተኛው ወሰነ-ትምህርት ስታተሳቸው Academic dismissal የሆኑ ተማሪዎች 1ኛ. ሽመልስ ሲሳይ (ከእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ-ፅሁፍ ፕሮግራም) 2ኛ. አባይነሽ ሹምዬ (ከፎክሎር ፕሮግራም) ትምህርታቸውን በprobation ለመቀጠል በፋካልቲው የደንበኞች አገልግሎት አስተባባሪ በኩል ለካውንስሉ ፈርመው አቅርበዋል፡፡ አስተባባሪውም እነዚህ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መቀጠል የሚችሉባቸው ሁለት አማራጮች ያሏቸው መሆኑንና የመጀመሪያው አማራጭ ከአንድ አመት በኋላ በዚያው በተባረሩበት ወሰነ-ትምህርት በመመለስ ዝቅተኛ ዉጤት ያገኙባቸውን ኮርሶች በመድገም ውጤታቸውን ማሻሻል ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ probation ማለትም ከአላፊ ተማሪዎች ጋር በቀጣዩ ወሰነ-ትምህርት ለባቻቸው የሚሰጡ ኮርሶችን በመውሰድ CGPAያቸውን ወደ 2፡00 ወይም ከዚያ በላይ ማሳደግ መሆኑን ለተማሪዎቹ መገለፁን ግልፀዋል፡፡ ተማሪዎቹም ይህን በመረዳት CGPAያቸውን ወደ 2፡00 ወይም ከዚያ በላይ ለማሳደግና ይህን ማድረግ ካልቻሉ ግን ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚባረሩ (complete dismissal እንደሚሆኑ) አውቀው የፕሮቤሽን ይሰጠን ጥያቄ አቅረበዋል፡፡ ካውንስሉም በጉዳዩ ላይ በጥልቀት በመወያየት በሌጅስሌሽኑ ላይ የተማሪዎቹን ዉጤት በተመለከተ cut-off point ስለሌለ የሁለቱንም ተማሪዎች ጥያቄ የተቀበለ ሲሆን በሌጅስሌሽኑ መሰረት ለተማሪዎቹ በፕሮቤሽን መቀጠላቸውን ለሚመጣዉ ዉጤት ሃላፊነቱ የራሳቸው መሆኑን በማሳሰብ ፈቅዶላቸዋል (ለዝርዝሩ አባሪ አንድና ሁለትን ይመልከቱ)፡፡

 

ስብሰባው በ5፡4ዐ ሰዓት ተጠናቋል ፡፡

የሰብሳቢ ፊርማ                                   የፀሐፊ ፊርማ

                                                                                                                ………………………..                               ……………………

Share