38ኛውን ዓመታዊ አለማቀፍ የግንቦት አውደ-ጥናት

 

የትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ኮሌጅ 38ኛውን ዓመታዊ አለማቀፍ የግንቦት አውደ-ጥናት አካሄደ
***************************************************************
በሙሉጌታ ዘለቀ
የትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ኮሌጅ 38ኛውን ዓመታዊ አለማቀፍ የግንቦት አውደ-ጥናት Ethiopia’s Progress towards achieving sustainable development በሚል ርዕስ በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንቦት 27 እና 28/2013 ዓ.ም አካሂዷል ፡፡
 
በአውደ-ጥናቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ለታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ እና ለኮንፍረንሱ አዘጋጆች የምስጋና መልእክታቸውን አስተላልፈው እንደሀገር የምንከተለው የትምህርት ስርዓት የመጭውን ትውልድ እጣ-ፋንታ የመወሰን ሀይል ስላለው በዋናነት ብቁ መምህራንን ከማፍራት አንፃር በመምህራን ስልጠና እና ትምህርት ስርዓቱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም የሴሚናሩ ተሳታፊዎች በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህረት ተቋማት የመጡ በመሆኑ ዶ/ር ፍሬው ስለባሕር ዳር ከተማና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አጠር ያለ ገለፃ አድርገዋል፡፡
 
 
በአውደ-ጥናቱ በኢትዮጵያ የUNESCO የትምህርት ዳይሬክተር የሆኑት Yumiko Yokozeki (PhD) በበይነ መረብ “The Role of Teachers in Achieving SDGs” በሚል ርዕስ ፁሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም የሳይንሰና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አማካሪና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ያለው እንዳወቀ “ Addressing quality education issues in higher education” ፣ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር አለማየሁ ቢሻው “Inclusive and equitable quality Secondary education” እንዲሁም የቀድሞ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩና በአሁኑ ሰዓት በእንግሊዝ ሀገር University of Cambridge የትምህርት ፋኩልቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር ዳዊት ጥበቡ “Understanding the impacts of large-scale educational reforms on primary school students learning progress: Who is benefiting from the reforms”? በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፁሁፎችን አቅርበው በተጨማሪም የአውደጥናቱን ጭብጥ አስመልክቶ ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
በዚህ ዓመታዊ አለማቀፍ አውደ-ጥናት ከ16 በላይ የሚሆኑ ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ታደሰ መለሰ በአውደጥናቱ መዝጊያ እንዳሉት የቀረቡት የጥናት ወረቀቶች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
 
በአውደ-ጥናቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ጥናትና ምርምር አቅራቢዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ባለሙያዎች፣ መምህራንና ተማሪዎች ታድመውበታል፡፡
 
በመጨረሻም በአውደ-ጥናቱ ላይ የጥናት ወረቀት ላቀረቡ መምህራን የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡